የጠላት ኢላማዎችን በአስተማማኝ ኹኔታ ለማውደም ከመቼውም ጊዜ በላይ ዝግጁ መኾኑን ምዕራብ ዕዝ አስታወቀ።

269

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 16/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ምዕራብ ዕዝ ጠላትን ድባቅ መምታት የሚችል የሜካናይዝድ ኀይል መገንባቱን አስታውቋል።

በምዕራብ ዕዝ የሜካናይዝድ ክፍሉ አስተባባሪ ኮ/ል ታደሰ ተበጀ እንደገለፁት የተኩስ አመራሩ እና የምድብተኛ ኀይሉ ያሳለፋቸውን የጦርነት ጊዜያት መነሻ ያደረገ በቂ ዝግጅት አድርገዋል፡፡

“በሁሉም የሜካናይዝድ ኃይላችን ወታደራዊ ስልጠናዎች ተካሒደዋል” ያሉት ኮ/ል ታደሰ የሜካናይዝድ ክፍሎች የሚሰጣቸውን ግዳጅ ተቀብለው የጠላትን ኀይል ድባቅ ለመምታት የላቀ የዝግጁነት ደረጃ ላይ እንደሚገኙ አብራርተዋል፡፡

“ሰራዊታችን ካካሔዳቸው ውጊያዎች በርካታ ልምዶችን በመውሰድ በሁኔታዎች መሃል በየጊዜው የሜካናይዝድ ኀይሉን የማድረግ አቅም ማሳደግ ችለናል” ብለዋል ኮ/ል ታደሰ ተበጀ ።

የሜካናይዝድ ክፍሎች ለእግረኛ ክፍለ ጦሮች የተኩስ ድጋፍ ለመስጠት እና የጠላት ኢላማዎችን በአስተማማኝ ኹኔታ ለማውደም ከመቼውም ጊዜ በላይ ዝግጁዎች ናቸው ሲሉ ገልፀዋል፡፡ መረጃው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ነው።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleማኅበረሰቡ በቀሪ ቀናት የያዘውን የጦር መሳሪያ በማስመዝገብ የአካባቢውን ሰላም እንዲጠብቅ የአማራ ክልል ሚሊሻ ጽሕፈት ቤት አሳሰበ።
Next articleʺየቀየውን ማሳ ሜዳና ዳገቱን ያርስ እንዳልነበረ፣ ዛሬ ዘመን ገፍቶት አራሹ ተሰዶ ማሳው ጦም አደረ”