የተቋማትን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ ሥርዓት የሚያዘምነው የኢትዮ ቴሌኮም ዘመናዊ የሞጁላር ማዕከል።

249

አዲስ አበባ: ግንቦት 12/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮ ቴሌኮም ዘመናዊ የሞጁላር ማዕከል ገንብቶ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በጋራ መጠቀም የሚያስችል ከፍተኛ አቅም ያለውን የመረጃ ማዕከል ስምምነት አካሄደ፡፡ ስምምነቱንም ዘመን ባንክ፣ ዘምዘም ባንክ፣ ሂጅራ ባንክ፣ ሬይስ ማይክሮፋይናንስ እና ዌብስፕሪክስ ጋር ነው ያካሄደው፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ እንደተናገሩት የመረጃ ማዕከሉ የተቋማቱን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ ሥርዓት ያዘምናል፤ ዓለም አቀፍ የጥራት ጀረጃውን በጠበቀ የመረጃ ማዕከል አማካኝነት አስተማማኝ እና ወጥ የኾነ አገልግሎት ለደንበኞቻቸው ለመስጠት ያስችላል፡፡

ዘመናዊ የመረጃ ማዕከሉ የራሱ የኾነ የኤሌክትሪክ ኃይል መጠባበቂያ አቅርቦት አለው ተብሏል፡፡ በሰለጠነ የሰው ኃይል የሚመራ እና አገልግሎቱ እንዳይስተጓጎል ከ90 በመቶ በላይ አስተማማኝ የኔትወርክ አቅም ያለው መሆኑንም ሥራ አስፈጻሚዋ ገልጸዋል፡፡

የመረጃ ማዕከሉ ለኩባንያዎች፣ ለአነስተኛ እና መካከለኛ የንግድ ተቋማት በሥራቸው ላይ ብቻ በማተኮር ተወዳዳሪ ምርታማ እንዲኾኑ ከፍተኛ አስተዋጾ አለው ተብሏል፡፡

ዘጋቢ፡-ራሄል ደምሰው

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleመተባበር አማራጭ የሌለው ምርጫ
Next article“በሐሰተኛ መረጃና ፕሮፖጋንዳ የዓለምአቀፉን ማኅበረሰብ ትኩረት ለመሳብ የሚደረግ ጥረት ቦታ የለውም” የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት