
ባሕር ዳር: ግንቦት 11/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በበጀት ዓመቱ 10 ወራት ከ282 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ገቢ በመሰብሰብ የእቅዱን 93 ነጥብ 15 በመቶ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን ገቢዎች ሚኒስቴር ገልጿል።
የገቢዎች ሚኒስቴር የተቋሙንና እና የጉምሩክ ኮሚሽን የበጀት ዓመት የ10 ወራት የሥራ አፈፃፀም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው እለት አቅርቧል።
በ2014 በጀት ዓመት የታክስ ፖሊሲና የታክስ አስተዳደር ማሻሻያዎችንና የኢኮኖሚ እድገት ትንበያን ታሳቢ በማድረግ 360 ቢሊዮን ብር ጥቅል እቅድ ተይዞ በ10 ወራት ውስጥ 175 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ከሀገር ውስጥ ገቢ፣ 127 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ከወጪ ንግድ ቀረጥና ታክስ በድምሩ 303 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ እቅድ በመያዝ ሥራ መጀመሩን የገቢዎች ሚኒስትሩ አቶ ላቀ አያሌው ገልጸዋል።
በመሆኑም ከሀገር ውስጥ ገቢ 168 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ወይም የእቅዱን 96 ነጥብ 23 በመቶ፣ ከወጪ ንግድ ቀረጥና ታክስ 113 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ወይም 89 በመቶ የተፈጸመ ሲሆን በድምሩ 282 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ገቢ በመሰብሰብ የእቅዱን 93 ነጥብ 15 በመቶ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን አብራርተዋል።
የ2014 በጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀም ከ2013 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወራት ጋር ሲነፃፀር የ44 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ወይም የ18 ነጥብ 63 በመቶ እድገት ማሳየቱንም ገልጸዋል። ዘገባው የኢብኮ ነው
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/