“ሀገር የምትቀድምባቸው፣ ወገን የሚከበርባቸው መኩሪያዎች”

209

ባሕር ዳር: ግንቦት 11/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ዓለማችን ላይ አንቱ የተባሉ ሀገራት የሚፈሩት እና የሚከበሩት በገነቡት የመከላከያ ሠራዊታቸው ነው፡፡ ሠራዊታቸውን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያጠነከሩ የሕዝባቸውን ህልውና የሚጠብቁትም ቁጥራቸው ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ በዘመናዊ ትጥቅ ስንቅ እና በአስተማማኝ ደጀንነት የቆመ መከላከያ ለሕዝብም ሆነ ለሀገረ መንግሥቱም የመውጫ መሰላል ነው፡፡ የምትፈራው እና የምትከበረው ባለህ የመከላከያ ሠራዊት አቅም ነው፡፡ በዓለም ላይ ያሉ ኀያላን ሀገራት አንዱ ሌላኛውን በልጦ ለመገኘት የማይሞክሩት ነገር የለም፡፡

የሀገራቱ የመከላከያ ጥንካሬም እርስ በእርስ እንዲፈራሩ እና እንዲከባበሩም አድርጓቸዋል፡፡ በዓለማችን ትልልቅ የመከላከያ ሠራዊት የገነቡ ሀገራት ለእድገታቸው መተማመኛ እየኾናቸው ነው፡፡ ሀገራቱ በጋራ ለመበልጸግ ከማሰብ እና ከመመካከር እና ከመደራደር አልፈው አንዱ የሌላኛውን የማልማት እና የእድገት እንቅስቃሴ ለማወክ ከሚያደረገው እንቅስቃሴ ሲቆጠብም ይስተዋላል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ መሳ ለመሳ ያለው የኀይል አሰላለፍ የግድ ያን እንዲያደርጉ ስለሚያስገድድ ነው፡፡

በመከላከያ አቅማቸው ደካማ የኾኑ ሀገራት ደግሞ በአንጻሩ የበላይ የኾኑ ሀገራት እንዳሻቸው ለማድረግ ሲጥሩ ነው የሚስተዋለው፡፡ የመልማት አቅማቸውም ከዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ ሁሌም ተመጽዋች እንዲኾኑ በኀያላኑ ሀገራት ተጽእኖ ሲደረግባቸው ይስተዋላል። ምንም እንኳን የተፈጥሮ ጸጋ እና ለመልማት የሚያስችል የጥሬ እቃ ባለቤት ቢኾኑም የኀያላኑ ሀገራት መጠቀሚያ ሲሆኑ ይስተዋላል። ይህን በመረዳትም የኀይል አቅሙን ያጠናከረ እና ለህልውናው ማስጠበቂያ የኾነውን መከላከያ ሠራዊት የገነባ ሀገር ተገዳዳሪ መሆን የሚችልበት እድልም ሰፊ ነው፡፡

ይህን ኀይል ለመገንባትም የዓለም ሀገራት ተሞክሮ እንደሚያሳየው የሀገራቱ ሕዝቦች ለመከላከያ ሠራዊታቸው የሚሰጡት ትኩረት እና አክብሮት ነው፡፡ ሕዝቡ መከላከያ ሠራዊት የሉዓላዊነቱ ምንጭ፣ የእድገቱ መሰረት እንደኾነ በመረዳት ይህን ኀይል ማጠናከር እና መደገፍ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይም ነው፡፡ በተለይ አንዳንድ ሀገራት እያንዳንዱ ዜጋ በመከላከያው ውስጥ የብሔራዊ አገልግሎት እንዲሰጥ ስለሚያደርጉ ሕዝቡ ለመከላከያ ኀይሉ ያለው እምነት፣ ተስፋ እና ፍቅር እንዲጨምር ያደርጋል፡፡

ኢትዮጵያዊያንስ ለመከላከያ ሠራዊታቸው ምንያክል ትኩረት ይሰጣሉ? ለኢትዮጵያዊያን እድገት እና ለሉዓላዊነታቸው መከበር የመከላከያ ሠራዊት ሚና በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ለመከላከያው ያለው እምነት፣ ተስፋ እና ፍቅር በአሸባሪው ትህነግ ቡድን አገዛዝ ጊዜ ሆን ተብሎ እንዲቀንስ ተደርጓል፡፡ አሸባሪው ቡድን በሕዝብ ትግል ከተወገደ በኋላም ሕዝቡ የጠላቶቹን ሴራ አምክኖ ደጀን በመኾን የመከላከያውን አቅም በመገንባት ላይ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ጥንተ ጠላቶች ይህን አጥር በማዳከም የሀገሪቱን ሀብት እንደለመዱት ያለከልካይ ዘግነው ለመውጣት እንዲያመቻቸው እና ጥቅማቸው እንዳይቀር መከላከያውን ማዳከም ዋና መንገድ እንደኾነ ተረድተው ከሕዝብ ሊነጥሉት ከፍተኛ ጥረትም አድርገዋል፡፡ ይሁን እንጅ መከላከያው በእሳት ውስጥ በማለፍ በደጀኑ ሕዝብ ታግዞ ጠንካራ አቋሙን እና አይበገሬነቱን በማሳየት የፈጸመው ተግባር የጠላት ቅስም እንዲሰበር አድርጓል፡፡

በተለይም አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ከውጭ ኀይሎች ጋር በመኾን መከላካያውን አዳክሞ ሀገሪቱን የትርምስ ማእከል ከማድረግ ባለፈ ለውጭ ጥንተ ጠላቶቿ ከፍቶ ለመስጠት የሄደበት እርቀት እና መከላከያው ራሱን በሕዝቡ ደጀንነት አጠናክሮ አሸናፊነቱን ያሳየበት ክስተት አንዱ ማሳያ ነው፡፡

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አሁን ላይ ያለበት ቁመና ጠላትን ለማሳፈር የሚያስችልበት ደረጃ መድረሱንም የሠራዊቱ አዛዦች እየተናገሩ ነው፡፡ የማዕከላዊ ዕዝ ኢንስፔክሽን ዳይሬክተር ኮሎኔል አብዱጀባር መሃመድ የሠራዊቱ አካላዊ፣ ሞራላዊ እና ሥነ ልቦናዊ ዝግጁነቱ የተሟላ ደረጃ ላይ መድረሱን ገልጸዋል፡፡

የግዳጅ ቀጠናን ተዘዋውረው የተመለከቱት ኮሎኔል አብዱጀባር የሠራዊቱ ትጥቅ፣ የአካል ብቃት፣ ሞራላዊ እና ሥነ-ልቦናዊ ዝግጁነቱ የተሟላ እንደኾነ ማየታቸውን ገልጸዋል።

ኮሎኔሉ እንዳሉት ሠራዊቱ ‟ላብ ደምን ያድናል” በሚል ተቋማዊ መርህ እየተመራ ቀን ከሌት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል የተሰጡትን ዘርፈ ብዙ ስልጠዎች በብቃት አጠናቆ በሁሉም መስክ ዝግጁ ሆኗል።

የማዕከላዊ ዕዝ ስልጠና ቡድን መሪ ተወካይ ሌተናል ኮሎኔል መላኩ አበጀ በበኩላቸው ተቋሙ ባወጣው የስልጠና እቅድ በመመራት እና የጠላትን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ ወታደራዊ ስልጠና በመውሰድ ጠንካራ ኀይል መገንባት መቻሉን ነው ያስገነዘቡት።

መከላከያ ሠራዊት ሊያጋጥመው የሚችለውን ማንኛውንም ጠላት መደምሰስ በሚያስችለው ወታደራዊ ዝግጁነት ላይ እንደሚገኝም ተገልጿል። ሠራዊቱ ወደፊትም በሕዝቡ ደጀንነት እየተመራ የተከበረችና ሕዝቦቿ ተከባብረው የሚኖሩባት ሀገር ለመገንባት እየሠራ ነው፡፡

በምሥጋናው ብርሃኔ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleሰዓተ ዜና ባሕር ዳር: ግንቦት 11/2014 ዓ.ም (አሚኮ)
Next articleበበጀት ዓመቱ 10 ወራት ከ282 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን የገቢዎች ሚኒስቴር ገለጸ።