“ሕዝቡን ወደ እርቅና ወደ ይቅርታ ማምጣት የሃይማኖት አባቶች ቀዳሚ ተግባር ሊሆን ይገባል” ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ

183

ባሕር ዳር: ግንቦት 10/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የእርቅን ጥቅም በመቀበል ወደ ተሻለ ነገር መራመድ ጊዜው የሚጠይቀው ተግባር መሆኑን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ገለጹ፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የ2014ን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ በከፈቱበት ወቅት ሕዝቡን ወደ እርቅና ወደ ይቅርታ ማምጣት የሃይማኖት አባቶች ቀዳሚ ተግባር ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡

ሰላም ለሃይማኖት መጠበቅና ለህዝብ ደኅንነት መረጋገጥ ትልቅ ዋጋ እንዳለውም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ አውስተዋል።

ሰው ሁሉ ሰላምን ቢጠብቅ በሁሉ ነገር ስኬታማ መሆን እንደሚቻል የገለጹት ፓትሪያርኩ በሀገሪቱ በተከሰቱ ግጭቶች ሕዝቡ መንገላታቱን ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ቅዱስ ጉባዔው ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ሰላም መሥራትና መጣር ይጠበቅበታል ነው ያሉት ብፁዕነታቸው፡፡

ሰላምንና አንድነትን ለማረጋገጥ የተከሰቱትን ችግሮች በውይይትና በድርድር ለመፍታት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ጥረት እንዲያደርጉም ፓትሪያርኩ ጥሪ አስተላልፈዋል። ዘገባው የፋብኮ ነው

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“ሙስናና ብልሹ አሠራርን ለመቅረፍ ቅንጅታዊ ሥራን ማጠናከር ይገባል” የፍትሕ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ.ር)
Next articleበኲር ጋዜጣ ግንቦት 8/2014 ዓ.ም ዕትም