
ግንቦት 10/2014 (አሚኮ) ሙስናና ብልሹ አሠራርን ለመቅረፍ በተናጥል የሚሠሩ ሥራዎች ብቻ በቂ ባለመኾናቸው ቅንጅታዊ አሠራር ማጠናከር ትኩረት ማድረግ እንደሚያስፈልግ የፍትሕ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ.ር) ተናገሩ።
ፍትሕ ሚኒስቴር ከሥነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ጋር በመኾን “የባለድርሻ አካላት የሙስና መከላከል ቅንጅት በኢትዮጵያ” በሚል መሪ ሐሳብ ምክክር እያካሄደ ይገኛል።
ውይይቱን አስመልክተው መልእክት ያስተላለፉት የፍትሕ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ.ር) ሙስናና ብልሹ አሠራር የማኅበረሰቡ አንገብጋቢ ችግር ኾኗል ብለዋል።
ሚኒስትሩ ሙስናና ብልሹ አሠራርን ለመቅረፍ በተናጥል የሚከናወኑ ሥራዎች ብቻ በቂ ባለመኾናቸው ቅንጅታዊ አሠራር ማጠናከር የግድ አስፈላጊ እንደኾነ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በውይይቱ የፌዴራል የሥነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ዶ.ር) ጨምሮ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የክልል የሥራ ኀላፊዎችና ተጋባዥ እንግዶች ታድመዋል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/