በ500 ሚሊየን ብር ወጭ በወረኢሉ ከተማ የግብርና ምርምር ማዕከል ሊገነባ ነው።

189

ባሕር ዳር: ግንቦት 09/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስትቲዩት በ500 ሚሊየን ብር 23ኛውን የግብርና ምርምር ማዕከል በአማራ ክልል ወረኢሉ ከተማ ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ አስቀመጠ፡፡

የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ዑመር ሁሴን እንደገለጹት የማዕከሉን ግንባታ በማዘመን የተሞክሮ ማዕከል እንዲሆን ይሠራል፡፡

የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስትቲዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ችሎት ይርጋ የግብርና ልማቱን ለማፋጠን የሚያስፈልጉ ቴክኖሎጂዎችን ለመፍጠር እና ለማላመድ የምርምር ማዕከላት ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ግንባታው ፍጥነት እና ጥራትን መሰረት አድርጎ በአምስት ዓመት ውስጥ እንደሚጠናቀቅም አመላክተዋል፡፡

በአማራ ክልል በምክትል ርእሰ መስተዳድር ማዕረግ የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ ወይዘሮ አይናለም ንጉሴ ከግብርና መር ወደ ኢንዱስትሪ መር ለሚደረገው ሽግግር የምርምር ማዕከሉ ግንባታ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleበኢትዮጵያ እና በቻይና ልማት ባንክ መካከል ያለው ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለጸ፡፡
Next articleበኢትዮጵያ ላይ የሚሰነዘረው የውጭ ተጽዕኖ ባለመቆሙ ሀገሪቱ የተጠናከረ የዲፕሎማሲ ሥራ እንደሚጠብቃት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመለከተ።