
ባሕር ዳር: ግንቦት 09/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በቻይና የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ከቻይና የልማት ባንክ የአሜሪካና አፍሪካ ዓለም አቀፍ ትብብር ዲፓርትመንት ጄኔራል ማናጀር ቢያን ሺዩዋን ጋር በዌቢናር ተገናኝተው ውይይት አድርገል። በውይይቱ በኢትዮጵያና በባንኩ መካከል ያለው ትብብር ለወደፊቱም በይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝና የአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ የራሱን አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳደረ ቢኾንም ኢኮኖሚው ይህን ጫና ተቋቁሞ በማደግ ላይ የሚገኝና ተስፋ ሰጪ መኾኑን አምባሳደሩ አስረድተዋል፡፡
ባንኩ በሂደት ላይ ላሉ የልማት ፕሮጀክቶችና ለሀገሪቱ የፋይናንስ ፖሊሲ ተቋማት የሚያደርገውን ድጋፍ በሀገሪቱ ቀጣይ የአስር ዓመት የልማት ዕቅድና በ8ኛው የቻይና አፍሪካ ትብብር ፎረም የሚኒስትሮች ኮንፈረንስ የልማት ትብብር ግቦች መሰረት አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።
የቻይና የልማት ባንክ የአሜሪካና አፍሪካ ዓለም አቀፍ ትብብር ዲፓርትመንት ጄኔራል ማናጀር ቢያን ሺዩዋን በበኩላቸው ባንኩ እንደ ፈረንጆቹ ከ2007 ጀምሮ የኢትዮጵያ ቁልፍ የልማት አጋር ኾኖ የቀጠለና ከሀገሪቱ የፋይናንስና የልማት ተቋማት ጋርም መልካም ትብብር ያለው መኾኑን ተናግረዋል።
ባንኩ ከኢትዮጵያ ጋር በሁለትዮሽና በባለብዙ ወገን የትብብር ዘርፎች ያለውን ግንኙነት አጠናክሮ ለመቀጠል ቁርጠኛ መሆኑን መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/