
ባሕር ዳር: ግንቦት 09/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ ሱዳን የያዘችባትን መሬት ለማስመለስ ለሰላም አማራጭ ቅድሚያ ሰጥታ እየሰራች መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተናገሩ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት የሚኒስቴሩን የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲያቀርቡ በጉዳዩ ላይ ለተነሳላቸው ጥያቄ በሰጡበት ምላሸ ነው።
የኢትዮ-ሱዳን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ስር የሰደደ መሆኑን ጠቅሰው፤ ሀገራቱ ረዥም ጊዜ ያስቆጠረውን የድንበር ጉዳይ በዘላቂነት ለመፍታት በጋራ ሲሠሩ መቆየታቸውን አስታውሰዋል።
ኢትዮጵያ በሰሜኑ የሀገሪቱ አካባቢ ሕግ የማስከበር ዘመቻ ላይ በነበረችበት ወቅት ሱዳን ድንበር በማለፍ ዜጎችን ያፈናቀለ፣ ሀብትና ንብረት ያወደመ ወረራ መፈጸሟን አስታውሰዋል።
በተጨማሪ በወረራ በያዘቻቸው አካባቢዎች ላይ የጂኦግራፊና ዲሞግራፊ ለውጥ ለማድረግ ፍጹም ተቀባይነት የሌለው ተግባር እየፈጸመች መሆኑን ገልጸዋል።
‘ኢትዮጵያ ችግሩን ለመፍታት የሰላም በር የተሻለ ነው’ በሚል የአፍሪካ ህብረትን ጨምሮ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጉዳዩን ሰንዳ ማቅረቧን ገልጸዋል።
ወረራው በሁለቱ ሀገራት መካከል ቅራኔ ከመፍጠር አልፎ ሌላ ችግር ሊያስከትል ስለሚችል አሁንም ኢትዮጵያ ለሰላም አማራጭ ቅድሚያ ሰጥታ እየሠራች መሆኑን ተናግረዋል።
ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እየተሰጠ ያለው ምላሽ የኢዮጵያን የሰላም አቋም የሚደግፍ ቢሆንም የሱዳንን ወረራ፣ ጠብ አጫሪነትና ኢ-ፍትሐዊነት በግልጽ ከማውገዝ አንጻር ዳተኝነት የተስተዋለበት መሆኑን አንስተዋል።
ኢትየጵያ ጉዳዩ የከፋ ጉዳት ሳያስከትል በሰላማዊ መልክ ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኝ አቋሟ ጠንካራ መሆኑን ገልጸው፤ በኅይል የተወረሩ መሬቶች መመለሳቸው አይቀሬ መሆኑን አረጋገጠዋል። ዘገባው የኢዜአ ነው
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/