ከኤርትራ ጋር የጋራ ጥቅሞቻችንን መሰረት በማድረግ በትብብር እየሰራን እንገኛለን – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን

195

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 09/ 2014 ዓ.ም (አሚኮ) ከኤርትራ ጋር የጋራ ጥቅሞቻችንን መሰረት በማድረግ በትብብር እየሰራን እንገኛለን ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸምን ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ እያቀረቡ ያሉት አቶ ደመቀ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ከጎረቤት አገሮች ጋር መልካም የሚባል ግንኙነት አላት።

ከኤርትራ ጋር የጋራ ጥቅምን መሰረት በማድረግ በትብብር እየተሰራ እንደሆነ ገልጸው፤ ግንኙነቱን ወደ ጠንካራ የኢኮኖሚ ትብብር ለማሸጋገር የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።

“የድንበር አካባቢ ንግድና የሰዎችን እንቅስቃሴ የሚያሳልጡ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች፣ የወደብ አጠቃቀም፣ የንግድ ልውውጥ፣ የጉምሩክ፣ የኢሚግሬሽንና የመሳሰሉ የሁለቱን አገሮች ሕዝቦች ተጠቃሚ ሊያደርጉ የሚችሉ የትብብር ማዕቀፎችን ለማበጀት ትኩረት ሰጥተን እየሰራን እንገኛለን” ብለዋል።

ኢዜአ እንደዘገበው በውጭ አገሮች የሚኖሩ የሁለቱ አገሮች ዳያስፖራዎች የተባበረ ድምጽ አወንታዊ ሚና እንደተጫወተም ገልጸዋል።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“ዲፕሎማሲያችን ላይ ያለውን ጫና ለመቋቋም ውስጣዊ አንድነታችንን ማጥበቅና መጠበቅ አለብን” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን
Next articleኢትዮጵያ ሱዳን የያዘችውን መሬት ለማስመለስ ለሰላም አማራጭ ቅድሚያ ሰጥታ እየሠራች ነው።