“ዲፕሎማሲያችን ላይ ያለውን ጫና ለመቋቋም ውስጣዊ አንድነታችንን ማጥበቅና መጠበቅ አለብን” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን

94

ግንቦት 09/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ዲፕሎማሲያችን ላይ ያለውን ጫና ለመቋቋም ውስጣዊ አንድነታችንን ማጥበቅና መጠበቅ አለብን ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን አስገነዘቡ።

አቶ ደመቀ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲያቀርቡ እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ በተለያየ መንገድ ጫና እየደረሰበት ይገኛል።

እየደረሰ ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ጫና በኢትዮጵያ ሕዝብ ጽናት፣ በዳያስፖራው ተሳትፎ እና በኢትዮጵያ ወዳጆች ትብብር መቋቋም መቻሉን አመልክተዋል።

ለዚህም አስተዋጽኦ ለመላው ሕዝብ፣ ለዳያስፖራውና ለኢትዮጵያ ወዳጆች ኹሉ ምሥጋና አቅርበዋል።

በጋራ ርብርቡ ጫናዎች የመለዘብ ምልክት ቢያሳዩም ጫናው በመቀጠሉ በትብብር መሥራቱ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል።

“የዓለም ሥርዐት ተገማች ያለመኾን፤ በተለያዩ ፍላጎቶችና የአሰላለፍ ለውጦች ምክንያት የዲፕሎማሲ ሥራችን በእጅጉ ፈተና የበዛበት ኾኖ መቀጠሉ አይቀሬ ነው” ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፤ ውስጣዊ አንድነታችንን ማጥበቅና መጠበቅ አለብን ብለዋል።

ሰላምን ከማረጋገጥ ሂደት ጎን ለጎን በማስገንዘብና በማለዘብ ላይ የተመሠረተ የውጭ ግንኙነትን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚጠይቅ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በጂኦ ፖለቲካ ፍላጎትና በልዩ ልዩ ውስጣዊ ኹኔታዎች ዲፕሎማሲው ተጽዕኖ ፈጣሪ ኾኖ ቀድሞ መንቀሳቀስ የሚፈለግበት ዘመን ላይ መድረሱንም ጠቁመዋል።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየሽብር ቡድኑ ዳግም የጦርነት ነጋሪት እየጎሰመ በመኾኑ ከመልሶ ግንባታው ጎን ለጎን የጥፋት ቡድኑን ዓላማ ለማክሸፍ በአንድነት መቆም እንደሚገባ የአማራ ክልል መንግስት አሳሰበ፡፡
Next articleከኤርትራ ጋር የጋራ ጥቅሞቻችንን መሰረት በማድረግ በትብብር እየሰራን እንገኛለን – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን