አርሶ አደሩ የክረምት የዝናብ ስርጭት ሁኔታን ተገንዝቦ በወቅቱ የግብርና ልማቱን ማከናወን እንዲችል ወቅታዊ የአየር ጠባይ ትንበያ በተገቢው መንገድ ተደራሽ እንዲሆን ማድረግ እንደሚገባ የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢታፋ አስገነዘቡ።

162

ባሕር ዳር: ግንቦት 08/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የበልግ ወቅት የአየር ጠባይ ትንበያ ግምገማና የመጪው የክረምት ወቀት የአየር ጠባይ ትንበያ ይፋ የሚደረግበት መድረክ ዛሬ በአዳማ በመካሄድ ላይ ነው።

የውኅና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢታፋ በመክፈቻው ላይ እንደገለፁት የበልግ ወቅት የአየር ሁኔታ ትንበያ በምስራቁ የሀገራችን ክፍል የተከሰተው ድርቅ በዜጎች ህይወት ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ቀድመን እንድንዘጋጅበት አድርጎናል ብለዋል።

በዚህም ድርቁ ያስከተለውን ችግር ለመቋቋም አቅም እንዲንገነባ ከማስቻሉም ባለፈ ሊደርስ የነበረውን አደጋ ማስቀረት እንዲንችል አግዞናል ብለዋል።

ባለፉት ስድስት ወራት የነበረው ድርቅ በማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት እንቃሴዎች ላይ ጫና ማሳደሩን የገለፁት ሚኒስትሩ ወቅታዊና ትክክለኛ የአየር ጠባይ ትንበያ ለህብረተሰቡ በማድረስ ረገድ አበረታች ውጤት መኖሩንም ተናግረዋል።

በቀጣይ ክረምት አርሶ አደሩ ሊኖር የሚችለውን የዝናብ ስርጭት ተከትሎ በአግባቡ እንዲጠቀም ለማድረግ ትክክለኛና ጥራት ያለውን ትንበያ ተደራሽ ማድረግ ላይ አሁንም ይበልጥ በትኩረት የሚንሰራበት ጉዳይ ነው ብለዋል።

አርሶ አደሩ የክረምት የዝናብ ስርጭት ሁኔታን ተገንዝቦ በወቅቱ የግብርና ልማቱን ማከናወን እንዲችል አሁንም ወቅታዊና ጥራት ያለው የአየር ጠባይ ትንበያ በተገቢው መንገድ ተደራሽ እንዲሆን ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስትቲዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ፈጠነ ተሾመ በበኩላቸው ለአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ ሴክተሮች ለይተን በትብብር እየሠራን ነው ብለዋል።

ዘመናዊ የሚቲዎሮሎጂ ቴክኖሎጂን ተጠቅመን በበልግ ወቅት የሚኖረውን የዝናብ ስርጭትና ሊፈጠሩ የሚችሉ ተፅዕኖዎች ላይ መሰረት ያደረገ የአየር ትንበያ ለተጠቃሚዎች ማድረስ መቻሉን ተናግረዋል።

በተለይ በመጪው ክረምት ትክክለኛ የአየር ንብረት ትንበያና መረጃ ተጠቃሚው ማኅበረሰብ ዘንድ እንደርስና የታሰበው ውጤት እንዲመጣ እየሠራን ነው ብለዋል።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“የዴሞክራሲ ባህል እንዲጎለብት እና ዘላቂ ሰላምና ፀጥታ እንዲሰፍን እንሠራለን” የፌዴሬሽን ምክር ቤት
Next articleበአማራ ክልል በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ በማቋቋሙ ተግባር ላይ ሁሉም የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲያደርግ ጥሪ ቀረበ።