“የዴሞክራሲ ባህል እንዲጎለብት እና ዘላቂ ሰላምና ፀጥታ እንዲሰፍን እንሠራለን” የፌዴሬሽን ምክር ቤት

170

ባሕር ዳር: ግንቦት 08/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የዴሞክራሲ ባህል እንዲጎለብት እና ዘላቂ ሰላምና ፀጥታ እንዲሰፍን እንደሚሠራ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ገለጸ፡፡

ምክር ቤቱ ከሁሉም ክልልና የሁለቱም ከተማ አስተዳደር የፍትህ አካላት ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት አድርጓል፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር ባስተላለፉት መልዕክት፥ ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ ውስጥ የዴሞክራሲ ባህል እንዲጎለብት፣ ዘላቂ ሰላምና ፀጥታ እንዲሰፍን፣ በዜጎች ዘንድ የሕገ መንግሥትና ፌዴራሊዝም እሳቤዎች እንዲሰርፁ፣ በፌዴራል መንግሥትና በክልሎች መካከል የሚከፋፈለው የጋራ ገቢዎች እና የፌዴራል መንግሥት ለክልሎች የሚሰጠው ድጎማ የሚከፋፈልበት ቀመር ይበልጥ ፍትሓዊ እንዲሆን ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ሕገ መንግሥታዊ መብቶችና ጥቅሞች እንዲረጋገጡ፣ በብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መካከል በመፈቃቀድ ላይ የተመሠረተ አንድነት ሥር እንዲሰድና እንዲዳብር በማድረግ በኩልም አበረታች ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የሚወከሉበት ቤት መሆኑን የጠቀሱት አፈጉባኤው ምክር ቤቱ የሕገ መንግሥቱ ጠባቂ የሆነ ሕገ መንግሥታዊ ተቋም እንደሆነም አመላክተዋል፡፡

የመድረኩ ዓላማ በሕገ መንግሥት ትርጉም ላይ ግንዛቤ ማሳደግ እንደሆነ መገለጹን ከፌዴሬሽን ምክር ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየጀግኖቻችንን የአብራክ ክፋዮች ዝቅ ብሎ ከፍ ማድረግ ኢትዮጵያዊ ግዴታ ነው!
Next articleአርሶ አደሩ የክረምት የዝናብ ስርጭት ሁኔታን ተገንዝቦ በወቅቱ የግብርና ልማቱን ማከናወን እንዲችል ወቅታዊ የአየር ጠባይ ትንበያ በተገቢው መንገድ ተደራሽ እንዲሆን ማድረግ እንደሚገባ የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢታፋ አስገነዘቡ።