መንግሥት የጀመረውን ሕግ የማስከበር እርምጃ አጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠየቀ።

210

አዲስ አበባ፡ ግንቦት 04/2014 ዓ.ም (አሚኮ) መንግሥት የዜጎችን ደህንነትና መብት ለማስጠበቅ የጀመረውን አጥፊዎችን ለሕግ የማቅረብ እርምጃና ችግሩ በሌላ ጊዜ እንዳይደገም ከመሠረቱ የመከላከል ሥራን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አቶ ኦባንግ ሜቶ ጠይቀዋል።

የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ኦባንግ ሜቶ በአገሪቱ የሕግ የበላይነትን በማስጠበቅ ዙሪያ ምን መደረግ አለበት በሚል ወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ እንደገለጹት፤ በኢትዮጵያ በየጊዜው እየታየ ያለውን የጸጥታ መደፍረስ ተከትሎ መንግሥት የጀመረውን የዜጎችን መብትና ደኅንነት የማስጠበቅ ኀላፊነቱን በአግባቡ መወጣት አለበት፤ በየጊዜው እየታየ ያለውን የጸጥታ መደፍረስ ለመከላከል የመንግሥት ዋና ሥራና ትኩረት የዜጎችን መብትና ደኅንነት መጠበቅ መኾን ይኖርበታል ብለዋል።

የመንግሥት ዋና ሥራና ትኩረት የዜጎችን መብትና ደኅንነት መጠበቅ ነው ያሉት አቶ ኦባንግ፤ በኢትዮጵያ ባለው ነባራዊ ሁኔታ አንዴ በሃይማኖት ሌላ ጊዜ በብሔር ሽፋን የሚከሰቱ ግጭቶች የደኅንነት ስጋት እየኾነ ይገኛል ሲሉ ገልጸዋል።

እንደ አቶ ኦባንግ ገለጻ፤ በኢትዮጵያ ታሪክ ተከባብሮና ተቻችሎ የመኖር እንጂ ሰዎች በማንነታቸውና በሃይማኖቸው ምክንያት የሚገደሉበትና የሚፈናቀሉበት ሁኔታ አልነበረም። አሁን ላይ ግን ይህ ሁኔታ ተቀይሯል። ይህም የሕግ የበላይነትን በአግባቡ ካለማስከበርና ኃላፊነትን በሚገባ ካለመወጣት የሚመጣ ችግር ነው።

የመንግሥት ኃላፊዎችና የጸጥታ አካሉ ሥራቸውን በአግባቡ ቢሠሩ ይህ ሁሉ እንደማይከሰት ገልጸው፤ የጸጥታ ኃይሎችና የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ኃላፊነት ወስደው የሕዝቡን ደህንነት በማስጠበቅ ለዘላቂ ሠላም መሥራት እንዳለባቸውም ነው የተናገሩት።

በተለይ ከሃይማኖት ጋር ተያይዘው ለሚነሱ ግጭቶች የሃይማኖት አባቶች ሥራቸው ሰዎች ከክፉ ነገር እንዲጠበቁ ማስተማር ቢኖርባቸውም፤ የዜጎችን ደህንነት የማስጠበቅ ኃላፊነት ያለው በዋናነት በመንግሥትና በጸጥታ ኃይሉ ላይ ነው ብለዋል።

ሕዝቡ ሠላምን ለማምጣት የራሱ ድርሻ ቢኖውም ኃይልና መሣሪያ ያለው መንግሥት እጅ እንደመሆኑ፤ የአገሪቷ ዋና ችግር የሆነውን የጸጥታ ችግር ጉዳይ መንግሥት በቅንነት ዜጎች እንዳይፈናቀሉና አላስፈላጊ ችግር ውስጥ እንዳይወድቁ ለግጭት መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ ችግሮች እንዳይከሰቱ ማድረግና ዜጎችን ለህልፈት የሚዳርጉ ወንጀለኞችን ለሕግ ማቅረብ እንዳለበት ተናግረዋል።

ፖለቲከኞችም ሀሳባቸውን ማቅረብ የሚችሉትም ሆነ ሌሎች ተግባራትን ማከናወን የሚቻለው የሰው በሕይወት የመኖር መብት እስከተጠበቀ ብቻ ነው ያሉት አቶ ኦባንግ፤ አጥፊዎችን ለፍርድ አቅርቦ እንዲጠየቁ ማድረግና ችግሩ በሌላ ጊዜ እንዳይደገም የመንግሥት ተግባር እንደተጠበቀ ሆኖ ሕዝቡም የበኩሉን ድርሻ ማበርከት እንደሚኖርበት ገልጸዋል።

አቶ ኦባንግ፤ «በመሪዎች ደረጃም ስለ ጠፋው የሰው ሕይወትና የደረሰው የንብረት ጉዳት ግልጽ መረጃ ለሕዝቡ መስጠት ይጠበቃል። የሃይማኖት ተቋማትም ሆኑ ሕዝቡ ሠላም እንዲኖር የራሳቸው ሥራ አላቸው። ከዚህ ባለፈ ግን እንዲህ ዓይነት ክስተቶች ሲፈጠሩ ከሕዝቡ ይልቅ መንግሥት ትልቅ ኃላፊነት አለበት። መንግሥት ከሁሉም አስቀድሞ የዜጎችን መብትና ደህንነት መጠበቅ አለበት» ብለዋል።

መረጃው የኢፕድ ነው።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“ሀገር ማጽናት ማለት በደም እና በአጥንት የሚረጋገጥ ነው” ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)
Next article“ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም የሌላት የአፍሪካ ዋንጫ መሥራች ሀገር “