አምስተኛው የምሥራቅ አፍሪካ የፋይናንስ ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

100

አዲስ አበባ፡ ግንቦት 03/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አምስተኛው የምሥራቅ አፍሪካ የፋይናንስ ጉባኤ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ ጉባኤው የምሥራቅ አፍሪካን የፋይናንስ ሥርዐት ማዘመን ላይ ያተኮረ ነው፡፡

በፋይናንስ ሴክተሩ ዙሪያ የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት እና ግዙፍ ድርጅቶች የሥራ ኀላፊዎች በቀጣናዉ የፋይናንስ ዙሪያ እየመከሩ ይገኛሉ ። በፋይናንስ ዘርፉ ተጽእኖ ከሚያሳድሩ ወሳኝ ዘርፎች የተውጣጡ የኢንዱስትሪ ባለሙያዎች፣ ተመራማሪዎች፣የባንክ ባለሙያዎች፣ ሥራ አስፈጻሚዎች፣ሥራ ፈጣሪዎች እና የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎችን ያካተተ መኾኑ ተገልጿል።

የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ መንግሥት በፋይናንስ ዘርፉ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል። ባለፉት ዓመታት የግሉ ዘርፉን በማበረታት የፋይናንስ ሴክተሩን ለማሻሻል ተሠርቷል ብለዋል። ፖሊሲዎችን የማሻሻል ሥራዎችም ተከናውነዋል ነው ያሉት፡፡

እንደ ኢትዮጵያ የፋይናንስ እና የመንግሥት ተቋማትን የተቀናጁ ለማድረግ እየተሠራ መኾኑን ገልጸዋል። አሁንም በግሉ ዘርፍ እና በመንግሥት ተቋማት መካከል ያለዉን ክፍተት ለመሙላት እንደሚሠራም ገልጸዋል፡፡ ጉባኤውም የተሻለ የፋይናንስ ሥርዐት በቀጣናዉ ለመዘርጋት የሚያግዝ መኾኑን ጠቅሰዋል። ጉባኤዉ ቅንጅታዊ አሠራርን በማጠናከር በወቅታዊ ተግዳሮቶች ላይ የመወያየት፣ የገበያ ስትራቴጅዎችን የመቅረጽ፣ ዕውቀትን የማጋራት እንዲሁም የነገዉን የፋይናንስ ዘርፍ ለመደገፍ የሚረዱ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ዓላማ ያደረገ መኾኑም ተነስቷል።

የዘንድሮዉን ጉባኤ ጅማ ዩኒቨርስቲ፣ የኢትዮጵያ መድን ሰጭዎች ድርጀት፣የተመሰከረላቸዉ የሒሳብ ባለሙያዎች ማኅበር እና the i-capital institute በጋራ አዘጋጅተውታል።

ዘጋቢ፡- ኤልሳ ጉዑሽ -ከአዲስ አበባ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ︎‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleለኢትዮጵያ የሚያስፈልገዉን የአፈር ማዳበሪያ መጠን ለማሳካት ከፍተኛ ጥረት መደረጉን የግብርና ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
Next article“ሀገር ማጽናት ማለት በደም እና በአጥንት የሚረጋገጥ ነው” ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)