ኢትዮጵያ እና ቱርክ በወንጀል መከላከል እና በወንጀል ጉዳዮች የጋራ የሕግ ትብብር ለማድረግ ስምምነቶችን ተፈራረሙ፡፡

110

ግንቦት 03/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የፍትሕ ሚኒስቴር የመንግሥት ሕግና ፍትሕ አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዓለምአንተ አግደዉ የተመራ የልዑካን ቡድን በቱርክ የሥራ ቆይታ አድርጓል፡፡ የልዑካን ቡድኑ በቱርክ የፍትሕ ሚኒስቴር በመገኘት በኹለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መክሯል፡፡

በውይይቱም የቱርክ ሪፐብሊክ መንግሥት የፍትሕ ሚኒስቴር ምክትል ሚኒስትር ያኩፕ ሞጉል በቱርክና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረ መኾኑን ገልጸዋል፡፡ በፍትሕ እና በወንጀል ጉዳዮች ላይ የሚደረጉ ትብብሮች አስፈላጊና ወንጀልን በመከላከል ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላቸዉ መኾኑን ተናግረዋል፡፡

በሀገራቱ መካከል የተለያዩ ትብብሮች ሲደረጉ የቆየ ቢኾንም በኹለቱ ሀገራት በዚህ ደረጃ የፍትሕ ትብብር ሰነዶች መፈረማቸዉ ግንኙነቱን የበለጠ ሕጋዊ መሠረት የሚሰጠዉ መኾኑን ጠቅሰዋል፡፡ በኹለቱ ሀገራት የሚፈለጉ ወንጀለኞችም በማንኛዉም ጊዜ በፍጥነት ተላልፈው መሰጠት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የፍትሕ ሚኒስቴር የመንግሥት ሕግና ፍትሕ አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዓለምአንተ አግደው በበኩላቸዉ ኢትዮጵያ ከብዙ ሀገራት ጋር በወንጀል ጉዳዮች ላይ በትብብር እንደምትሠራ ገልጸዋል፡፡

ከቱርክ መንግሥት ጋር በወንጀል ጉዳዮች ላይ የሚደረገው የጋራ ስምምነትም በኹለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የረጅም ጊዜ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግረዉ መኾኑን ጠቅሰዋል፡፡

በቀጣይ በጋራ በመሥራት ትብብሩን በማጠናከር ረገድ ትኩረት እንደሚሰጥ የኹለቱም ሀገራት ተወካዮች ገልጸዋል፡፡

በሀገራቱ መካከል በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችን አሳልፎ ለመስጠት እና በወንጀል ጉዳዮች የጋራ የሕግ ትብብር ለማድረግ የሚያስችሉ ስምምነቶች መፈረማቸውን ከፍትሕ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመላክታል።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየአማራ ክልል መንግሥት በሕግ ማስከበሩና በህልውና ዘመቻው ተሳትፎ ላደረገው የጸጥታ መዋቅር የእውቅና እና የምስጋና መርሃ ግብር ዛሬም ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎችና የመከላከያ ሠራዊት መሪዎች በተገኙበት እየተካሄደ ነው።
Next articleለኢትዮጵያ የሚያስፈልገዉን የአፈር ማዳበሪያ መጠን ለማሳካት ከፍተኛ ጥረት መደረጉን የግብርና ሚኒስቴር ገለጸ፡፡