የአማራ ክልል መንግሥት በሕግ ማስከበሩና በህልውና ዘመቻው ተሳትፎ ላደረገው የጸጥታ መዋቅር የእውቅና እና የምስጋና መርሃ ግብር ዛሬም ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎችና የመከላከያ ሠራዊት መሪዎች በተገኙበት እየተካሄደ ነው።

736

ባሕር ዳር: ግንቦት 03/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት “በሕግ ማስከበርና በህልውና ዘመቻው የተከፈለ መስዋእትነት ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እና አንድነት” በሚል መሪ መልእክት በሕግ ማስከበሩና በህልውና ዘመቻው ተሳትፎ ላደረገው የጸጥታ መዋቅር የእውቅና እና የምስጋና መርሃ ግብር ዛሬም የፌድራል ከፍተኛ ኀላፊዎች፣ የክልል ርእሳነ መስተዳደሮች፣ ሚኒስትሮች በተገኙበት በማካሄድ ላይ ነው።

የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በምክትል ርእሰ መስተዳደር ማዕረግ የአስተዳደር ጉዳዮች ክላስተር አስተባባሪ ዶክተር ሰማ ጥሩነህ በዛሬው መርሃ ግብር አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ሀገር ለማፍረስ በአማራና በአፋር ክልሎች የፈፀመውን ወረራ በመቀልበስ ትልቅ ተጋድሎ ለፈጸሙ ጀግኖች እውቅና ይሰጣቸዋል ብለዋል።

ኢትዮጵያዊያን በፍጹም ሀገራቸውን አስደፍረው አያውቁም፣ አሁንም ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚፍጨረጨሩ ሁሉ ተስፋ ቆርጠው አርፈው እንዲቀመጡ አስረግጠን እንነግራቸዋለን ነው ያሉት በንግግራቸው።

የአማራ ሕዝብ ለሀገሩ አንድነት ፅኑ ዓላማ ያለው መሆኑን የምናረጋግጥበት ዝግጅት ነውም ብለዋል።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleበኩር ጋዜጣ ግንቦት 01/2014 ዓ.ም ዕትም
Next articleኢትዮጵያ እና ቱርክ በወንጀል መከላከል እና በወንጀል ጉዳዮች የጋራ የሕግ ትብብር ለማድረግ ስምምነቶችን ተፈራረሙ፡፡