
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 27/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌዴሪ ጦር ኀይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀነራል አበባው ታደሰ በኅልውና ዘመቻ ወቅት ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን ቆመው በሙያቸው ሲያገለግሉና መስዕዋነት ጭምር ሲከፍሉ ለነበሩ የጤና ባለሙያዎች ሠራዊቱን ወክለው ምስጋና አቅርበዋል።
ለጤና ባለሙያዎችና ለተለያዩ የተቋማት በባሕርዳር ከተማ እየተደረገ በሚገኘው የእውቅናና የምስጋና መድረክ ላይ ተገኝተው ነው ምስጋናውን ያቀረቡት።
በየጤና ተቋማቱ ተዘዋውረን ታዝበናል ያሉት ምክትል ኤታማዦር ሹሙ “ለሙያቸውና ለሀገራቸው ታማኝ የኾኑ እና ከሰራዊቱ ጋር ለ24 ሰዓት ሳይታክቱ የሚሰሩ ባለሙያዎችን በመመልከቴ ለክልሉና ለሀገርም ኩራት የሚሆኑ የጤና ባለሙያዎች እንዳሉን አረጋግጫለሁ” ብለዋል።
“የጤና ባለሙያዎችና ተቋማት ድርብ ሀላፊነትን ይዘው እየሠሩ ነበር” ያሉት ምክትል ኤታማዦር ሹሙ በጠላት የተጎዱ የማህበረሰብ ክፍሎች ከማከም በተጨማሪ የመከላከያ ሰራዊቱን የመንከባከብ ሀገራዊ ጫና ውስጥም እንደነበሩ ገልፀዋል። በዚህም የጤና ባለሙያዎችና ተቋማት ማይረሳ ታሪክ እንደጻፉና የሀገር መከላከያ ሰራዊትም ከፍ ያለ ምስጋና እንደሰጠ ገልጸዋል።
በቀጣይም የጠላት ሀሳብ ጨርሶ እስከሚቀበር ድረስ የክልሉ ጤና ባለሙያዎች ከመከላከያ ሰራዊት ጎን ቆመው የተለመደ ሀገራዊ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡም ጀነራል አበባው ተናግረዋል።
ዘጋቢ:- አሚናዳብ አራጋው
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/