የቀደሙት አባቶች በዱር በገደል ተዋድቀው ነፃ ያቆዩንን ሀገር አንድነቷን ጠብቆ ማስቀጠል እንደሚገባ በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር አባት አርበኞች ተናገሩ፡፡

146

እንጅባራ: ሚያዝያ 27/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የጀግኖች አርበኞች ድል መታሰቢያ በዓል በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር በእንጅባራ ከተማ እየተከበረ ነው፡፡

የቀደሙት የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ብሄር፣ ቋንቋ፣ ሃይማኖትና መሰል ጉዳዮች ሳይለያቸው የጣሊያንን ጦር ለአምስት ዓመታት ተጋድለው በጠላት ያልተንበረከከች ነፃ ሀገር አስረክበዋል፡፡

እነኾ የጀግኖች አርበኞች የድል መታሰቢያ በዓል በየዓመቱ ሚያዝያ 27 እየተዘከረ 81 ዓመታትን ዘልቋል፡፡

81ኛው የጀግኞች አርበኞች ድል ቀን መታሰቢያ በዓልም በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር እንጅባራ ከተማ በጎዳና ላይ ሰልፍና መፈክሮችን በማሰማት እየተከበረ ነው፡፡

በበዓሉ የታደሙት አባት አርበኞችም የአኹኑ ትውልድ የቀደሙት አባቶች በዱር በገደል ተዋድቀው ነፃ ያቆዩትን ሀገር አንድነቷን ጠብቆ የማስቀጠል ታሪካዊ ኀላፊነት አለበት ብለዋል፡፡

ዘጋቢ፡-ሳሙኤል አማረ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleዝክረ ሸዋረገድ ገድሌ – ጀግኒት ኢትዮጵያዊት አርበኛ!
Next articleአርበኛ ማን ነው? አርበኝነትስ ምንድን ነው?