በአፋር ክልል የተለያዩ ከተሞች ሠላማዊ ሠልፎች እየተካሄዱ ነው፡፡

231

ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 6/2012 ዓ.ም (አብመድ) ከአፋር ክልል ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክትው በአፋር ክልል የተለያዩ ከተሞች ሠላማዊ ሠልፎች እየተካሄዱ ነው፡፡ ሠመራንና አዋሽ ሰባት ኪሎን ጨምሮ ከሠሞኑ ሰልፍ ባልተካሄደባቸው ከተሞች ሕዝቡ ዛሬ ወደ አደባባይ መውጣቱ ነው የተገለጸው፡፡

ሠልፈኞቹ የአፋር ክልል ላይ በውጭ ኃይሎች በተለይም አልሸባብ የሚፈጸም ጥቃት እንዲቆምና የፌዴራል መንግሥት ሉዓላዊነትን እንዲያስከብር መጠየቃቸው ነው የተገለጸው፡፡

በአፋር ክልል ከሰሞኑ በተፈፀመ ጥቃት በርካቶች በተለይም ሴቶችና ሕጻናት ሕይወታቸው ማለፉንና የቆሰሉም መኖራቸውን መዘገባችን የሚታወስ ነው፡፡

ዘጋቢ፡- አብርሃም በዕውቀት
ፎቶ፡- ከአፋር ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት

Previous articleበቀጣዩ ሃገር አቀፍ ምርጫ ላይ የሚሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሴቶች ተሳትፎ ትኩረት እንዲሰጡ ተጠየቀ፡፡
Next articleኢትዮጵያ ኢኮኖሚዋን ለማሳደግ ከጎረቤት እና ከዓባይ ተፋሰስ አባል ሀገራት ጋር ያላትን የግንኙነት ፖሊሲ በጥንቃቄ መቅረጽ እንዳለባት ተመላከተ፡፡