“እንደሀገር የገጠሙንን ፈተናዎች በፅናት በመሻገር ለመጪው ትውልድ ነጻ፣ ሰላማዊ እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ለማውረስ ዳር እስከዳር አንድነታችንን ማጥበቅ እና መጠበቅ ይገባናል” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን

111

ሚያዝያ 27/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን 81ኛው የአርበኞች ቀን መታሰቢያ በዓል አስመልክቶ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ያስተላለፉት መልዕክት ቀጥሎ ቀርቧል:-

ለመላው የሀገራችን ሕዝብ!

ለ81ኛው የአርበኞች ቀን መታሰቢያ በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ፤ አብሮ አደረሰን።

የአርበኞች ቀንን በልዩ ትኩረት እና ክብደት የምንዘክረው ጀግኖች አርበኞች ለሀገር አንድነት እና ሉዓላዊነት መከበር የከፈሉትን ዋጋ በትውልዱ ዘንድ ተምሳሌታዊ የድል አድራጊነት መንፈስ እንዲጋባ በማሰብ ነው።

ታሪክ በከፍታ እንደሚገልጸው ጀግኖች አርበኞች በእናት ሀገር ላይ የተቃጡ ጥቃቶችን በመመከት እና በጠላት ላይ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ አኩሪ ድሎችን ተቀዳጅተው ነፃና ሉዓላዊት ሀገር አስረክበዋል።

በተለይ ጀግኖች አርበኞች ሀገራችንን ከወራሪ ጠላት ለመጠበቅ በዱር በገደል በመዋደቅ እና አኩሪ ገድል በመፈጸም በትውልድ ቅብብሎሽ የድል አድራጊነት ዘላቂ ፈለግ አውርሰው አልፈዋል።

በዚህ ረገድ ዘንድሮ ለ81ኛ ጊዜ በኩራት የምንዘክረው “የአርበኞች ቀን” ሀገራችን ያለችበት አኹናዊ ኹኔታ ተከትሎ፤ ለትውልዱ የሚቸረው ታሪካዊ ትርጉም በእጅጉ የተለየ ያደርገዋል።

በአኹን ጊዜ በመላው ሀገሪቱ ሰላም እና ፀጥታን በዘላቂነት ከማስፈን አኳያ ለጀመነው ትግል የቀደሙ ጀግኖቻችንን የድል አድራጊነት ፅኑ መንፈስ ለትውልዱ በማውረስ ረገድ ታሪካዊ ፋይዳው እጅግ የላቀ ነው።

እንዲሁም በዜጎቻችን ላይ የተጋረጡ ማኅበረ~ኢኮኖሚያዊ ጫናዎችን የሚያቀሉ የልማት ውጥኖቻችን በፍጥነት ለማረጋገጥ ከጀመርነው ኹሉአቀፍ ርብርብ አኳያ፤ “የአርበኞች ቀን” የሚያላብሰን ተምሳሌታዊ ትጋት እና ወኔ በልዩነት እና በከፍታ የሚታይ ነው።

እንደሀገር የገጠሙንን ፈተናዎች በፅናት በመሻገር ለመጪው ትውልድ ነጻ፣ ሰላማዊ እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ለማውረስ ዳር እስከዳር አንድነታችንን ማጥበቅ እና መጠበቅ ይገባናል።

በዚህ አጋጣሚ የቀደሙ ጀግኖቻችንን የድል አድራጊነት ታሪክ፤ ዘመኑ በሚጠይቀን የትግል አውድ ላይ ለመድገም ከመቼውም ጊዜ በተሻለ ፅናት በጋራ እንድንቆም አደራ ለማለት እወዳለሁ።

መልካም የድል በዓል!

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article‘‘ምን ዓይነት ወኔ ነው፤ ምን ዓይነት ድፍረት መድፍ የጨበጠውን በድንጋይ መምታት!’’
Next article“…ቀደምት ዐርበኞች ላከበሯት ሀገራችን ልዕልናና ብልጽግና ለማጎናጸፍ ዋጋ የምንከፍል ተተኪ ዐርበኞች መኾናችንን ልናረጋግጥ ይገባናል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)