
ሚያዝያ 26/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ጦርነት የከፈተው እና የአማራ እና የአፋር አካባቢዎችን ወርሮ ከፍተኛ ሰባዊ እና ቁሳዊ ውድመቶችን ያደረሰው አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ለሚያደርገው ተጨማሪ ወረራ እና ውድመት ለመዝመት ያልፈለጉ ልጆች ወላጆችን እያሰረ እንደሚገኝ የቤተሰብ አባላት ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ቢቢሲ ያነጋገራቸው አንድ የትግራይ ተወላጅ ለመዝመት ፍቃደኛ ሳይኾን በመቅረቱ ወላጅ አባቱ እና አጎቱ እንደታሠሩ ገልጿል።
ለራሱና ለቤተሰቡ ደኅንነት ሲል ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀው ወጣት፤ “ቢያንስ ከቤተሰብ አንድ ሰው ለውትድርና መላክ የሚል ሕግ አውጥተው እየተንቀሳቀሱ ነው” ብሏል።
ልጆቻቸውን ወደ ጦር ሜዳ ባለመላካቸው አጎቱም ጭምር ለእስር መዳረጋቸውን የሚናገረው ወጣቱ ከሁለት ወር በፊት አጎቱ 18 ዓመት ያልሞላት ሴት ልጁን እንዲያመጣ ተጠይቆ ፈቃደኛ ባለመኾኑ አስረውት እንደነበር አስረድቷል። ወላጆቹ እና ቤተዘመዱ አሁን ያሉበትን ሁኔታ ለማወቅ አስቸጋሪ እንደኾነም ነው የገለጸው፡፡
በአሁኑ ጊዜ የትግራይን ክልል እያስተዳደረ ያለው አሸባሪ ህወሀት ለመዝመት ፍቃደኛ ያልኾኑ ልጆች ወላጆችን ማሰር ከመጀመሩ በፊት ሰዎችን አስገድዶ ወደ ጦር ሜዳ ይልክ እንደነበርም ተናግሯል።
ወጣቶችን አስገድዶ ለማዝመት ሙከራ አድርጎ ያልተሳካለት የሽብር ቡድኑ ‘ወላጆችን በማሰር ወደ እኩይ ዓላማው ይገባሉ በሚል እስሩን አጠናክሮ መቀጠሉን አስረድቷል፡፡ እንደ ሕግ የወረደው አሠራርም በትግራይ ምድር በጣም ችግር መፍጠሩን ነው ያስገነዘበው።
በክልሉ የሚንቀሳቀሰው የተቃዋሚ ፓርቲ አባል አቶ ክብሮም በርሀ በሽብር ቡድኑ ወረራ ባለመሳተፋቸው ወላጆቻቸው እንደታሰሩባቸው ተናግረዋል።
የባይቶና ዓባይ ትግራይ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ክብሮም በርሀ ታናሽ እህታቸው በወረራው ለመሳተፍ ባለመፈለጓ ወላጅ እናታቸው መታሰራቸውን ነው ለቢቢሲ የገለጹት። “እኛ ቤት ሁሉም ስደት ላይ ናቸው” ብለዋል አቶ ክብሮም።
አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ከዚህ በፊት ልጆች አልዘመቱም በሚል ወላጆችን እንደሚያስር ማመኑን ቢቢሲ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስነብቧል፡፡
በምስጋናው ብርሃኔ
( ከታች የተያያዙት ምስሎች በአማራ እና አፋር ግንባሮች የተማረኩ የሽብር ቡድኑ አባላት ናቸው። )
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/