
ሚያዝያ 26/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ኤች አር 6600 እና ኤስ 3199 የተሰኙትና በአሜሪካ የተወሰኑ የሴኔት አባላት የተዘጋጁት የማዕቀብ ረቂቅ ሕጎች ሂደት እና እንቅስቃሴን በንቃት እየተከታተለ መኾኑን ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል፡፡
ፓርቲው ረቂቅ የማዕቀብ ሕጎቹ ቢጸድቁ የሚያስከትሉትን ተጽዕኖ እና ረቂቅ ሕጎቹን ለማዘጋጀት ያስፈለገበትን ዓላማ በጥንቃቄ እና በተከታታይ መመርመሩን ገልጿል፡፡
በአሜሪካ እና በኢትዮጵያ መካከል ለዘመናት በዘለቀው የዲፕሎማሲ እና የሁለትዮሽ ግንኙነት አብን የተለየ ክብር እና ዋጋ አለው ያለው መግለጫው ይህንን የሁለቱን ሀገራት ታሪካዊ ግንኙነት እና የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ይሠራል ነው ያለው፡፡
አብን በመግለጫው የአሜሪካ መንግሥት ለኢትዮጵያ ሰላም፣ መረጋጋት እና ዲሞክራሲ ያለውን ቁርጠኝነት አድንቆ በሀገሪቱ ለተፈጠረው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ምክንያት የኾኑ ሁሉ ተጠያቂ መኾን እንደሚገባቸው ያምናል ብሏል፡፡ ነገር ግን ሰላምን፣ መረጋጋትን እና ዲሞክራሲን ለማምጣት ግራ አጋቢ እና ስላቅ የሚስተዋልበት የማዕቀብ ሕግ መፍትሄ ሊኾን አይችልም ነው ያለው፡፡
መግለጫው ረቂቅ የማዕቀብ ሕጎቹ የከፋ ደም መፋሰስን፣ መቆሚያ የሌለው ግጭትን እና የከፋ አምባገነናዊ ሥርዓትን ከመፍጠር ውጭ የተሻለ መፍትሄ እንደማያመጡ ጠቅሶ በሀገሪቱ በተፈጠረው ችግር ተጎጂዎችን እና ጥፋተኞችን በአንድ የሚያይ በመኾኑ ጉዳቱ ሀገራዊ ነውና ተገቢነቱ ላይ እንደማያምን አብን አስታውቋል፡፡
ኢትዮጵያ ከቅኝ ግዛት እና ከውጭ ወራሪ ኅይሎች ተደጋጋሚ ተፅዕኖ ራሷን ጠብቃ የዘለቀች ሀገር ናት ያለው አብን ዛሬም የትኛውንም ዓይነት የውጭን ኀይል ተፅዕኖ እና ጣልቃ ገብነት የሚቀበል ትውልድ አይኖርም ብሏል፡፡ በመኾኑም በቅጥረኛ ኀይሎች ግፊት እና የጥቅም ትስስር ወደ ረቂቅ ሕጎቹ ተሳትፎ የገቡ የሴኔት አባላት ለደረጃቸው እና ለሀገራቸው ክብር ስለማይመጥን ራሳቸውን በጊዜ ከዚህ ሂደት እንዲያወጡ አብን በመግለጫው ጠይቋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት ረቂቅ የማዕቀብ ሕጎቹ እንዳይጸድቁ የሚጠበቅበትን ሁሉ እንዲያደርግ ያሳሰበው የአብን መግለጫ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ኤች አር 6600 እና ኤስ 3199 ረቂቅ የማዕቀብ ሕጎችን በመቃዎም በጋራ እንዲቆሙም ጥሪ አቅርቧል፡፡
ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
