በቀጣዩ ሃገር አቀፍ ምርጫ ላይ የሚሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሴቶች ተሳትፎ ትኩረት እንዲሰጡ ተጠየቀ፡፡

195

ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 5/2012 ዓ.ም (አብመድ) የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባዔ ወይዘሮ ሽታዬ ምናለ የፊንላንድ ፓርላማ ልዑካን ቡድን እና መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት አባላትን ዛሬ በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አወያይተዋል፡፡

በውይይቱም ፊንላንድ በኢትዮጵያ ለሚካሄደው ለውጥ ሙሉ ድጋፏን እንደምትሰጥ ተገልጿል፡፡ የለውጥ ሂደቱ ከዚህ በበለጠ ሁሉን አቀፍ እንዲሆን ሊሰራበት እንደሚገባም ሀሳብ ሰጥተዋል፡፡

ምክትል አፈ-ጉባዔ ወሮ. ሽታዬ ምናለ በበኩላቸው በቀጣዩ ሀገር አቀፍ ምርጫ ላይ የሚሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሴቶች ተሳትፎ በትኩረት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።

ለዚህም አሁን ከፊንላንድ የመጡት እና ሌሎች መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ድጋፍ ከማድረግ ባለፈ ተፅዕኖ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡

ምንጭ፦ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት

Previous articleብቸኛው ከአዲስ አበባ-ደሴ-ወልዲያ-ትግራይ መተላለፊያ ድልድይ ተገልጋዮችን እያማረረ ነው፡፡
Next articleበአፋር ክልል የተለያዩ ከተሞች ሠላማዊ ሠልፎች እየተካሄዱ ነው፡፡