
ሚያዝያ 25/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በሕዳሴው ግድብ እና በከፍተኛ የፋይናንስ ተቋማት ላይ ያነጣጠሩ የሳይበር ጥቃቶች መክሸፋቸውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አሥተዳደር ገለጸ።
የሀገሪቱን ሰላም እና ዕድገት በማይፈልጉ ሀገራት የሚደገፍ ድርጅት የሕዳሴው ግድብ ግንባታን ለማስተጓጎል በማቀድ ‘ብላክ ፒራሚድ ዎር’ በሚል ስያሜ የሳይበር ጦርነት መክፈቱን የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አሥተዳደር ዋና ዳይሬክተር ሹመቴ ግዛው (ዶ.ር) ተናግረዋል።
ይኹንና የጥፋት ዓላማ አቅደው ሲያሴሩ የነበሩት ኹሉ እንዳሰቡት ሕልማቸው ሳይሳካ ተጨናግፏል ብለዋል።
የፋይናንስ ተቋማት የሚጠቀሙባቸው እና እርስ በርሳቸው የተሳሰሩ 37 ሺህ ኮምፒውተሮችን ላይ ጥቃት በመፈጸም የሕዳሴው ግድብን ለማስተጓጎል እንደተሞከረም ገልጸዋል።
ጥቃቶቹም በኢንፎርሜሽን ደኅንነት አሥተዳደር ጥብቅ ክትትል ምንም ጉዳት ሳያስከትሉ እንዲቋረጡ እና እንዲመክኑ መደረጋቸውን አስታውቀዋል።
የሕዳሴው ግድብ ኃይል ማመንጨት ከጀመረ በኋላ የሚሰነዘሩ የሳይበር ጥቃቶች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚችል ይገመታል ያሉት ዶክተር ሹመቴ ከዚህ በኋላም የሳይበር ምኅዳሩን በመጠቀም ግድቡ በአግባቡ ኃይል እንዳያመነጭ እና እንዲቆም ጥረት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል ብለዋል። ለዚህም ጠንካራ የሳይበር ደኅንነት ተግባራዊ በማድረግ ከሕዳሴው ግድብ ግንባታ እና ቁጥጥር ተቋማት ጋር በቅርበት እየተሠራ መኾኑን ጠቁመዋል።
ግድቡን በተመለከተ ከአመራረት እስከ ግንባታ ዕቃዎች ማጓጓዣ የሚያጠቃልሉ ሥራዎች ላይ የሳይበር ምኅዳሩን በመጠቀም ከፍተኛ ክትትል ይደረጋልም ብለዋል።
በሕዳሴው ግድብ ላይ የሚቃጡ የሳይበር ጥቃቶች እስካኹን ምንም ዓይነት ጉዳት ሳያደርሱ እንዲመክኑ ቢደረግም አሁንም የፋይናንስ ተቋማት ላይ ተመሳሳይ ጥቃቶች እየተሰነዘሩ መኾኑን አስታውቀዋል።
እንደ ኢነርጂ ተቋማት ኹሉ ፋይናንስ ተቋማትም በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚደረጉ የሳይበር ጥቃቶች ዒላማ መሆናቸውን ነው የገለጹት።
የሳይበር ጥቃቶችን ለመከላከል ኹልጊዜም አንድ እርምጃ ቀድሞ ማየት፣ ማቀድ እና መተግበር ያስፈልጋል ማለታቸውን የኢፕድ ዘገባ ያመለክታል።
በፋይናንስ ተቋማት ላይ የሚሰነዘሩ የሳይበር ጥቃቶች ሰብረው መግባት ከቻሉ መዘዛቸው ብዙ እንደኾነ የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሩ፣ የተቃጡት ጥቃቶች ቢሳኩ ኖሮ በፋይናንስ ተቋማት ላይ ብቻ ሳይኾን በሀገር ደረጃ ከፍተኛ ችግር ያስከትሉ እንደነበር ገልጸዋል።
የፋይናንስ ተቋማቱ ከነዚህ ዓይነት ጥቃቶች ራሳቸውን ለመጠበቅና ለመከላከል አስፈላጊ የሚባሉ ዝግጅቶችን ማድረግ አለባቸው ሲሉ አሳስበዋል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/