የአፋር ክልል ርእሰ መሥተዳድር አወል አርባ የኢድ በዓልን አስመልክቶ ማዕድ አጋሩ።

178

ሰመራ: ሚያዝያ 24/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአፋር ክልል ርእሰ መሥተዳድር አወል አርባ የኢድ አልፈጥር በዓልን አስመልክቶ በሰመራ ከተማ ተጠልለው ለሚገኙ 5 ሺህ ለሚደርሱ ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለው ለሚገኙ ዜጎች ማዕድ አጋርተዋል ።

በዚህ ወቅት ርዕሰ መሥተዳድሩ እንኳን አደረሳችሁ ብለው ጁንታው በአፋር ላይ ያደረሰው ወረራ በታሪክ አይረሳም፤ በጀግንነትና በጋራ ጥረታችን መክተን ዛሬ ጁንታው ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶበት ወደ ኋላ አፈግፍጓል ብለዋል። ይህ የኾነው በአንድነትና በትብብር ፤ በሀገር ወዳድነት በመቀናጀታችን ነው ይህም የኢድ በዓልን ስናከብር ልንደግመው የተቸገሩትን ልንደግፍና በዓሉን ደስ ብሎአቸው እንዲያሳልፍ መኾን አለበት ነው ያሉት።

በቀጣይ ተፈናቃዮችን ወደ ቋሚ መኖሪያ ቀያቸው መመለስ የክልሉ መንግሥተ ትኩረት መኾኑን ገልፀዋል።

የሠመራ መጠለያ የኢድ በዓል ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ አሊ ሁሴን በክልሉ ከሠመራ በተጨማሪ በአፍዴራ፣ በጉያህ፣ በዱብቲ፣ በአሳይታ እና በሌሎች አካባቢዎችም መሠል ተፈናቃዮችን የኢድ በዓል ማዕድ ማጋራት እየተካሄደ እንደኾነ ገልፀዋል።

ዘጋቢ:- ሰለሞን አደላ – ከአፋር ሰመራ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“ሕዝበ ሙስሊሙ ሊከባበር፣ ሊፈቃቀር እና አንድነት ሊኖረው ይገባል” ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር እድሪስ
Next article“በአማራ ክልል ኹሉም አካባቢዎች 1443ኛው ዓመተ ሂጅራ የዒድ አልፈጥር በዓል የሶላት ሥነ-ሥርዐት ሰላማዊ በሆነ መልኩ ተከናውኗል” የአማራ ክልል መንግሥት