“ሕዝበ ሙስሊሙ ሊከባበር፣ ሊፈቃቀር እና አንድነት ሊኖረው ይገባል” ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር እድሪስ

174

አዲስ አበባ: ሚያዚያ 24/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ሕዝበ ሙስሊሙ ሊከባበር፣ ሊፈቃቀር እና አንድነት ሊኖረው እንደሚገባ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር እድሪስ ጥሪ አቀረቡ።

ሐጂ ሙፍቲ ይህን ጥሪ ያቀረቡት በአዲስ አበባ ስታዲየም እየተከበረ በሚገኘው የኢድ ሰላት መርኃግብር ላይ ባደረጉት ንግግር ነው።

በንግግራቸውም አንድነት፣ ሰላም፣ ልማት፣ ዕድገት ኹሌም ለኢትዮጽያ አስፈላጊ መኾኑን አስገንዝበዋል።

አንድነት በተግባር የሚገለጽ በመኾኑ ኹሉም ለአንድነት የሚችለውን ኹሉ ማበርከት እንዳለበት ገልጸዋል።

መንግሥት ለሙስሊሙ ማኅበረሰብ እያደረገ ላለው ትብብር እና ትኩረትም ምሥጋና አቅርበዋል።

የንጹሐን ደም መፍሰስ የለበትም፣ ንጹሐንም መፈናቀል የለባቸውም ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼክ ሱልጣን አማን ኤባ በበኩላቸው የዘንድሮውን ረመዳን ከዒድ እስከ ዒድ ጥሪን ተከትለው ከመጡ ኢትዮጵያውያን ጋር ስናከበር ቆይተናል ብለዋል።

ሰሞኑን በተለያዩ አከባቢዎች በተፈጠረው ችግር እጃቸው አለበት የሚባሉትን መንግሥት ለሕግ ሊያቀርባቸው እንደሚገባ ገልጸዋል።

በሀገሪቷ የሚታየው አለመግባባትም በውይይት እና መግባባት ሊፈታ እንደሚገባም ማሳሰባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ታላቁ የዒድ ስግደት በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ ይገኛል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም በመከበር ላይ በሚገኘው ታላቅ የዒድ ስግደት የእስልምና የእምነት አባቶች፣ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች፣ ከጎረቤት ሀገራት የመጡ እንግዶች፣ ዳያስፖራዎች፣ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላት እና የእምነቱ ተከታዮች በመሣተፍ ላይ ይገኛሉ።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“ረመዳን በኢትዮጵያ ፍቅርና ሀገራዊ አንድነት የታየበት በመሆኑ ከመቼም ጊዜ የተለየ ተደርጎ በታሪክ ሲታወስ ይኖራል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
Next articleየአፋር ክልል ርእሰ መሥተዳድር አወል አርባ የኢድ በዓልን አስመልክቶ ማዕድ አጋሩ።