ኢጋድ፣ ጤና ሚኒስቴር እና ጎንደር ዩኒቨርስቲ አብረው ለመሥራት ተፈራረሙ።

226

ሚያዝያ 23/2014 ዓ.ም (አሚኮ)የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በየነ-መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) በኅብረተሰብ ጤና ግንዛቤ ማሻሻያ ሥራዎችና ምርምር ዙሪያ አብሮ ለመሥራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ከኢፌዲሪ የጤና ሚኒስቴርና ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጋር ተፈራርሟል።

ስምምነቱን የፈረሙት የኢጋድ ዋና ጸሓፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ.ር)፣ የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ እና የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አሥራት አፀደወይን (ዶ.ር) ናቸው።

ስምምነቱ በምሥራቅ አፍሪካ በየነ-መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) አስተባባሪነት የሚከናወኑ የጤና እና ጤና ነክ ሥራዎች በሀገራት መካከል ያለውን ትብብር በማጎልበት በለጋሽ ድርጅቶች ደጋፊነት በድንበርና ድንበር ተሻጋሪ በሽታዎች ቁጥጥር አማካኝነት የጤናውን ዘርፍ ማጠናከር ተቀዳሚ ዓላማው አድርጎ የሚሠራ ይኾናል።

ወደ ተግባር በሚገባበት ጊዜም ዘርፈ ብዙ ምላሽ በመስጠት የኅብረተሰቡን የጤና ንቃት የማሳደግ እና ምርምሮችን የመሥራት ዓላማ አጣምሮ መያዙን ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተገኘ መረጃ ያመላክታል።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleጉባኤው ድብቅ ፍላጎት ያላቸው ግለሰቦች ሃይማኖቶችን ሽፋን በማድረግ ያልተገባ ድርጊት እንዲፈጸም እያደረጉ መሆኑን ገለጸ።
Next article“ረመዳን በኢትዮጵያ ፍቅርና ሀገራዊ አንድነት የታየበት በመሆኑ ከመቼም ጊዜ የተለየ ተደርጎ በታሪክ ሲታወስ ይኖራል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ