ጉባኤው ድብቅ ፍላጎት ያላቸው ግለሰቦች ሃይማኖቶችን ሽፋን በማድረግ ያልተገባ ድርጊት እንዲፈጸም እያደረጉ መሆኑን ገለጸ።

98

አዲስ አበባ፡ ሚያዝያ 23/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ድብቅ ዓላማና ፍላጎት ያላቸው ግለሰቦች ሃይማኖቶችን ሽፋን በማድረግ ያልተገባ ድርጊት እንዲፈጸም እያደረጉ መኾኑን የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አስታወቀ፡፡

ጉባኤው ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1 ሺሕ 443ኛው ዓመተ ሂጅራ የኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል።

ጉባኤው ባወጣው መግለጫ ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር በሀገሪቱ እየሆነ ስላለው ክፋትና በደል በመጸጸት እውነተኛ ንስሀ በማድረግ ወደ ፈጣሪው በመጠጋት ሊሆን እንደሚገባ ገልጿል።

ግጭት እና ግድያ አሁንም እንደቀጠለ መሆኑን ያስታወቀው መግለጫው ድብቅ አላማና ፍላጎት ያላቸው ግለሰቦች ሃይማኖቶችን ሽፋን በማድረግ ያልተገባ ድርጊት እንዲፈጸም እያደረጉ ሲሆን ለዘመናት ተከባብሮ የኖረውን ሕዝብ አንዱ በሌላው እንዲነሳና አለመተማመን እንዲፈጠር እያደረጉ መሆኑን አመላክቷል።

የዘንድሮውን በዓል ስናከብር ከውጭ ሀገር ወደ ሀገራቸው በመግባት ላይ ለሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ደማቅ አቀባበል ማድረግ እንደሚገባ መግለጫው አስታውሷል።

መግለጫው ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር እስልምና በሚያስተምረው መሰረት የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳትና ያለውን በማካፈል እንዲሆን አሳስቧል።

በወቅታዊ ሁኔታው ተፈናቅለው ከመኖሪያቸው ርቀው በችግር የሚገኙ ወገኖችን በማሰብ እንዲሆን ጉባኤው በመግለጫው አሳስቧል።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“የዒድ-አልፈጥር በዓልን ስናከብር ሃይማኖታዊ አስተምህሮቱ እና ሕግጋቱ በሚያዘውና በሚፈቅደው መሠረት የተፈናቀሉና የተቸገሩ ወገኖቻችን በማሰብ እንድናሳልፍ ጥሪዬን አቀርባለሁ” ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)
Next articleኢጋድ፣ ጤና ሚኒስቴር እና ጎንደር ዩኒቨርስቲ አብረው ለመሥራት ተፈራረሙ።