
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 23/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ለመላው እስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ለ1443ኛው ዒድ- አልፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ርእሰ መሥተዳድሩ ያስተላለፉት መልዕክት ቀጥሎ ቀርቧል:-
የረመዳን ጾም መስዋእትነትን በትዕግሥት መሻገርን፣ በትዕግሥት ለመልካም ነገር መነሳትን፣ በትሕትና ፈተናን ማለፍን፣ በመታዘዝ ሃይማኖታዊ ሥነ-ምግባር ጠብቆ የሚፆምበት ወቅት ነው።
የጾም ፍጻሜ ደግሞ ዒድ አልፈጥር ነው። ዒድ – አልፈጥር ደግም ምረቃ ነው።
በዓሉ ጥልቅ መንፈሳዊ እሴቶች የሚዳብሩበት፣ ከሌሎች ሃይማኖት ተከታዮች ጋር በመተሳሰብ እና በመረዳዳት በአንድነት የሚያሳልፉት በዓልም ነው፡፡
ይኽን በሕዝቦች መካከል አብሮ የኖረውን የመቻቻል፣ የመፈቃቀድ፣ የአንድነት እሴት በማጎልበት አንድነታችን ጠብቀን ኑረናል፤ ወደፊትም አጠናክረን እናስቀጥላለን።
ስለኾነም የዒድ-አልፈጥር በዓልን ስናከብር ሃይማኖታዊ አስተምህሮቱ እና ሕግጋቱ በሚያዘውና በሚፈቅደው መሠረት የተፈናቀሉና የተቸገሩ ወገኖቻችን በማሰብ እንድናሳልፍ ጥሪዬን እያቀረብኩ በዓሉ የሰላም፣ የደስታ፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ እና የአንድነት እንዲኾንላችሁ መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ።
ዒድ ሙባረክ!
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/