
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 23/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል መንግሥት ለመላው የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ለኢድ አልፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል።
የክልሉ መንግሥት ያስተላለፈው መልዕክት ቀጥሎ ቀርቧል:-
““ኢድ ሙባረክ””!!!
የረመዳን ወር መላው ሙስሊሞች በጾም፣ በሶላት፣ በዱዓ፣ ምጽዋትን በመለገስና ከፈጣሪ ዘንድ ምህረትን በመማጸን፤ ከምድራዊው ዓለም ይልቅ ለመጭውና ለወዲያኛው ዓለም ሕይወት ስኬትን ለማግኘት በሚረዱ መንፈሳዊ ተግባራት ላይ በመሳተፍ አሳልፋችሁ የአምልኮ ምንዳዎቻችሁን ከዓለማት ፈጣሪ የምትመነዱበት ታላቅ ወር ነው፡፡ በመኾኑም እንኳን ለዚህ ታላቅ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡ ኢድ ሙባረክ!!!
ምንም እንኳ ባሳለፍነው የረመዷን ወር ኢትዮጵያዊ የመተሳሰብ ባህልን ያላሳዩ ሁኔታዎች የተስተዋሉበት፤ የሰው ልጅን ክቡር ሕይወት፣ አካልና ንብረት ያወደሙ ግጭቶች መስተዋላቸው እሙን ቢኾንም ሙዕሚን እና ሙዕሚናቱ የተፈጠሩ ግጭቶችን በእርቅ፣ በይቅርታና በፍቅር መርህ በመሻገር የቀደመ የአብሮነት እሴቶቻችንን ለማጽናት ላሳያችሁት ቀናዒነት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የላቀ አክብሮት አለው፡፡
ይህ ወቅት እንደ ሀገር ተፈጥሯዊ እና ሰው ሠራሽ በኾኑ ተከታታይ ቀውሶች እየተደራረቡ የተመላለሱበት ወቅት እንደመኾኑ መጠን የመሻገሪያ መንገዳችንም በእኩልነት የተመሰረተ አንድነት ላይ በምንገነባው ኢትዮጵያዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት መኾኑን ከታሪካዊ ተሞክሯችንም ኾነ ከነባራዊ ሁኔታዎቻችን መረዳት ይቻላል፤ ይገባናልም፡፡
ስለኾነም በአማራ ክልል የምትኖሩ ኢትዮጵያዊ ሙስሊሞች በክልላችን ሰላም፣ ልማት፣ እኩልነት እና ሀገራዊ አንድነትን በሕዝቦች መካከል ለማጽናት እንደ አንድ የሀገር ባለቤት እንደኾነ የኅብረተሰብ ክፍል ገደብ የለሽ አስተዋጽኦችሁን እንድታበረክቱ እየጠየቅን በዓሉ የመተሳሰብ፣ የሰላም፣ የደስታና የሀሴት እንዲኾንላችሁ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ልባዊ ምኞቱን ለመግለጽ ይወዳል።
“ኢድ ሙባረክ”
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
ሚያዚያ 23/2014 ዓ.ም
ባሕር ዳር
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/