
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 23/2014 ዓ.ም (አሚኮ) እኛ ኢትዮጵያውያን እንደ ሀገር ያጋጠሙንን ችግሮች ለመሻገር ሙስሊሙ እና ክርስቲያኑ ማኅበረሰብ ለዘመናት በአብሮነት መኖራችን ትልቁን አስተዋፅኦ አበርክቶልን እንዳለፈ መታወቅ አለበት ሲሉ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ኢድሪስ ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ኢድሪስ የ1443ኛውን የኢድ- አልፈጥር በዓል ምክንያት በማድረግ ለሕዝበ ሙስሊሙ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በመልዕክታቸውም ሕዝበ ሙስሊሙ በረመዳን ወር ያዳበራቸውን መልካም ስራዎች ከረመዳን ውጪ ባሉት ወራትም የተራቡትን በማብላት፣ የታረዙትን በማልበስና የተቸገሩትን በመርዳት እንዲሁም የማዕድ ማጋራቱን ስራ በቀጣይነት በመፈፀም ከፈጣሪው የሚያገኘውን ምንዳ ከፍ ማድረግ ይኖርበታል ብለዋል፡፡
አክለውም በረመዳን የሰራናቸውን መልካም ተግባራት ሁሉ ከበዓሉም በኋላ ከዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያችን ጋር በማቀናጀት ኢስላማዊ ሰብዕናችንን አድምቀን መታየት ይገባናል ብለዋል፡፡
ከረመዳን ወር ፆም መጠናቀቅ ጋር ግዴታ የሚሆነው ” ዘካተል ፊጥር ” የተደነገገበት የእስልምና ዋና ዓላማ ሁሉም ሙስሊም ድሃ ሰዎችን ከመለመን እንዲድኑና በዕለቱ እንደማንኛውም ሰው እኩል ሆነው የበዓሉ ተካፋይ እንዲሆኑ ለማስቻል መሆኑም ገልጸዋል፡፡
በአሁን ሰዓት አገራችን በታላቅ ለውጥ ላይ እንደምትገኝ ኹላችንም እንረዳለን ያሉት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ኢድሪስ በሀገራችን ብሄራዊ መግባባትን ለማምጣት የተጀመረውን ጥረት ሁላችንም ልናግዝ ይገባል ብለዋል፡፡
በመኾኑም ያለንን ፀጋ እንደ ጥሩ አጋጣሚ ተጠቅመን የተጀመረውን ለውጥ ለእድገትና ለሰላም እንድናውለው፤ በጥንቃቄና እና በትዕግስት እንድንይዘው በታላቅ አክብሮት እጠይቃለሁም ነው ያሉት፡፡
ሰሞኑን የተከሰተው አስከፊ ሁኔታ ዳግም መደረግ ቀርቶ መታሰብ እንደሌለበት ጠቁመው በድርጊቱ የተሳተፉ አካላትም ለሕግ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል፡፡
በዓሉ የሰላምና የደስታ እንዲኾንልን መልካም ምኞቴን እገልፃሁ “ኢድ ሙባረክ” ሲሉ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/