
አዲስ አበባ: ሚያዝያ 22/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር የሥራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የአምራች ኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም ለማሳደግ ከባለድርሻ አካላት ጋር የንቅናቄ መድረክ በአዲስ አበባ እያካሄደ ነው።
በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደተናገሩት እድገት ያለ ጥረት እና ድካም ከቶውንም አይታሰብም። የዕድገት ራዕያችን ማጥራት፣ ለሥራ ያለንን ፍቅርና ትጋት ማሳደግ፣ ጊዜያችንን እና ሃብታችንን በአግባቡ ማሳደግ ይገባል ብለዋል።
የከፍታ ማማ ላይ ወጥተው የምናያቸው ሀገራት የከፍታቸው መነሻ ለኢንዱስትሪው ክፍለ ኢኮኖሚ የሰጡት ከፍተኛ ትኩረት ነው ብለዋል ከንቲባዋ።
የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ዣንጥራር ዓባይ በበኩላቸው ድህነት የሚጠፋው ስለተፀየፍነው እና ደጋግመን ስላወራንለት ሳይኾን የድህነት ምንጮችን በመለየት፣ በመተባበር እና ሥራን ትንሽ ትልቅ ሳንል በርትተን ስንሠራ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
“የሀገሮች ኹሉ የዕድገት ልዩነት ምክንያት ኢንዱስትሪ ነው። አምራች ኢንዱስትሪ የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት፣ የውጭ ጫናንን በመቀነስ፣ ከውጭ የሚገባን ምርትን በመተካት በአጠቃላይ ዘላቂነት ያለው ሀገራዊ ዕድገት ለማምጣት ሚናው የጎላ ነው” ብለዋል።
የመንግሥት ፖሊሲ ጥራት እና አተገባበር ችግር ለዘርፉ ዕድገት ማነቆ እንደኾነ የገለፁት ምክትል ከንቲባው እንቅፋት የኾኑ ፖሊሲዎችን መፈተሽ እና ዘርፉን መደገፍ አለብን ነው ያሉት።
“መሪዎች ሕዝባዊ ነን ካልን የሚከለክለውን ሳይኾን የሚፈቅደውን ሕግ አስቀድመን ዘርፉን እናበረታታ” ብለዋል።
ዘጋቢ:- በለጠ ታረቀኝ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/