
ባሕር ዳር ፡ ሚያዝያ 21/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ለአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) እንዳብራሩት የገበያውን ፍላጎት ያገናዘበ ፣እውቀትና ክህሎት ያለው፣ የሰለጠነና ተወዳዳሪ የኾነ የሰው ኀይል ለማፍራት እየተሠራ መኾኑን ገልፀዋል።
ሚኒስትሯ ሥራ አጥነትን ለመቀነስ ጥናትን መሰረት ያደረገ ተግባር እየተከናወነ ስለመኾኑም ተናግረዋል።
የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመን በሚሠሩ ጉዳዮች ላይ በሙያው የበቁ፤ ክህሎት ያላቸው ሰዎችን ለመፍጠርም እየተሠራ እንደኾነ አስታውቀዋል።
የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ የሥራ ፈጣሪነት አስተሳሰብ ግንባታ ላይ፣ የሙያ ደኅነትና ጤንነት፣ የኢንዱስትሪ ሰላም ላይ ውጤት ሊያመጣ የሚያስችል ቅንጅታዊ አሠራር ተዘርግቷል ብለዋል፡፡
ሚኒስትሯ በቴክኒክና ሙያ ተቋማት የሚፈጠሩ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በማሸጋገርና ጥቅም ላይ በማዋል ለሥራ እድል ፈጠራው አጋዥ እንዲኾኑ በትኩረት እየተሠራ መኾኑን አንስተዋል። በአዳዲስ የሙያ ዘርፎች ላይ ውጤታማ ተግባር እየተከናወነ እንደኾነም ተናግረዋል፡፡
ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከእቅዱ በአማካይ ከ85 እስከ 95 በመቶ ስኬት የታየባቸው፣ መቶ በመቶም አፈጻጸም ላይ የተደረሰባቸው ዘርፎች እንዳሉም ተናግረዋል።
የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የቢዝነስ ሃሳብ መፍለቂያ እንዲኾኑ፣ ተማሪዎቻቸው ተመርቀው ከወጡ በኋላ ሳይሆን እዛው እያሉ ሥራንና አሠራርን ይዘው የሚወጡበት መንገድ እንዲፈጠር በጋራ እየተሠራ መኾኑን አስታውቀዋል።
ዘጋቢ፡-ጋሻው አደመ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/