
ጎንደር: ሚያዝያ 21/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በጎንደር ከተማ አስተዳደር በተከሰተው ችግር 373 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ደሳለኝ ጣሰው አስታውቀዋል።
አቶ ደሳለኝ ስለ ጎንደር የፀጥታ ሁኔታ መግለጫ ሰጥተዋል። በሰጡት መግለጫ ጎንደር ያለ ታሪኳና ያለ ባሕሏ ችግር መከሰቱን አስታውሰዋል። ጎንደር ላይ በተፈፀመው ችግር ምክንያትም ችግሮቹን እንዲሰፉ የሚያደርጉ አካላት መኖራቸውን ገልፀዋል። ጥፋተኞቹን የመያዝ ተግባርም እየተሠራ ነው ብለዋል።
ከሀገር ሽማግሌዎች፣ ከሃይማኖት አባቶች እና ከሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር በመወያየት ወደ ሰላም ከተመለሰ በኋላ ትናንት እንደገና እኩይ ዓላማቸውን ለማስፈጸም ፍላጎት በነበራቸው አካላት በተነሳ ግጭት የሰው ሕይወት ማለፉንና ንብረት መውደሙን አስታውቀዋል።
ትናንት ዳግም ግጭት ለመቀስቀስ የሞከሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውንም ገልፀዋል። በተወሰደው እርምጃ ጎንደር ወደ ሰላም እየተመለሰች ነው፤ አስተማማኝ የሚሆነው ግን በጥፋት የተሳተፉትን በሙሉ ለቅመን ስንይዝ ነውም ብለዋል።
ይሕ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ የፀጥታ ኃይሉ በሠራው ሥራ 373 ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገልጿል።
ኃላፊነታቸውን ያልተወጡ የፀጥታ ኃይሎችንና መሪዎችን በሕግ ተጠያቂ እየተደረገ መሆኑንም ገልፀዋል።
የፀጥታ ኃይሉ በተቀናጀ መንገድ እርምጃ እንዲወስድ አቅጣጫ መቀመጡንም አስታውቀዋል። ኃላፊነቱን ያልተወጣ ሁሉ ይጠየቃል ነው ያሉት። የፀጥታ ኃይሉም ስምሪት ላይ ነው ብለዋል።
ተጠርጣሪዎች ተለቅመው እስኪያዙ ድረስ ከፀጥታ ኃይሉ ውጭ ያለው መሣሪያ እንዳይወጣ አቅጣጫ ተቀምጧል።
የፀጥታ ኃይሎችን ልብስ ከአባል ውጭ ለብሶ በሚገኝ አካል ላይ እርምጃ እንደሚወሰድም ገልፀዋል።
ከከተማ የሚወጣም ሆነ የሚገባ መሣሪያ እንዳይኖር ታግዷልም ነው ያሉት። ከሕዝብ ጋር የሚቆሙትና ለሕዝብ መስዋእትነት የሚከፍሉ የራሳቸው ትጥቅ ያላቸው ጀግኖች ፋኖዎች ከመንግሥት ሥምሪት እስከሚሰጣቸው ድረስ በቤታቸው ሆነው እንዲጠብቁም ጥሪ አቅርበዋል። በፋኖ ስም በሚነግድ አካል ግን አስፈላጊው እርምጃ ይወሰዳል ነው ያሉት።
ለአንድ ወገን በማድላት ችግር እንዲባባስ የሚያደርጉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም አሳስበዋል።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/