
ሚያዝያ 21/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የደቡብ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በስልጤ ዞን በአንዳንድ አካባቢዎች በሃይማኖት ተቋማት ላይ የደረሰውን ጥቃት አወግዟል።
የደቡብ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ፓስተር ተሰማ ታደሰ ትናንት ሚያዝያ 20/2014 ዓ.ም በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ እና በሳንኩራ ወረዳ በሃይማኖት ተቋማት ላይ የደረሰውን ጥቃት አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፣ ድርጊቱን የፈጸሙ ኀይሎች ላይ መንግሥት አስፈላጊውን እርምጃ ሊወስድ ይገባል ብለዋል።
በእስልምና እና በክርስትና ቤተ እምነቶች መካከል ለረጅም ዘመናት የቆየ መቻቻል እና መከባበር እሴት ያላስደሰታቸው አካላት ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ በቤተ እምነቶች እና በምዕመናን ላይ ያነጣጠረውን ጥቃት በክልሉ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ስም አውግዘዋል።
ኅብረተሰቡ በሀገራችን በየትኛውም አካባቢ እና በየትኛውም የእምነት ተቋማት ላይ የሚቃጣውን ጥቃት መመከት እንዳለበትም ጥሪ አቅርበዋል።
በክርስትና እና በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚታየው መቻቻል እና አብሮነት ለሌሎች ሀገሮችም በአብነት የሚጠቀስ ነው ያሉት ፓስተር ተሰማ በቤተ እምነቶች መካከል ያለው ሰላም አንድነት እና መቻቻል መጠናከር እንዳለበትም በመግለጫቸው ጠቁመዋል።
ሰሞኑን በጎንደር አካባቢ የተከሰተው የሃይማኖት ተቋማት እና የምዕመናን ጥቃት በምንም ሁኔታ ተቀባይነት የለውም ሲሉም አብራርተዋል፤ ይህንንም አስመልክቶ ድርጊቱን ማውገዛቸውንም ገልጸዋል።
በወራቤ አካባቢ የመቻቻል እና የመደጋገፍ እሴት በምሳሌነት የሚጠቀስ እንደኾነም መግለጻቸውን የደቡብ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መረጃ ያመለክታል።
የነበረውን መልካም እሴት መገለጫ ለመመለስ መሥራት ይገባልም ብለዋል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/