የልብ ወግ!

155

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 21/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ድሮ እያሉ ማውራት ተለምዷል፡፡ ሕዝብም ያፍ አመል ኾነና ድሮ እኮ እንዲህ አልነበረም ሲል ይደመጣል። ለመሆኑ ዛሬ ለምን ድሮ መሆኑ ቀረ ቢሉ ምላሹ ብዙ ነው፡፡ የፍቅር ጥግ ሲሸረሸር ትናንት ዛሬን መኾን ያቅተዋል፡፡
የሰው ልጅ ሲማር ሲመራመር የበለጠ በሰወኛ ባሕሪው ይለመልማል ሲባል ይባሱን ወደታች እያሸቆለቆለ ተራራውን ወደታች ለመውደቅ እየተንደረደረ ነው፡፡ ተራራውን ለመውጣት ግን ሰፊ ጥረት፣ መቻቻል እና በአንድነት ገመድ መሳሳብን ይፈልጋል፡፡
ኢትዮጵያ በልጆቿ የአንድነት ገመድ ተገምዳ ሥትሠራ የሃይማኖቶች ገመድ ትልቅ ሚና አለው፡፡ ይህ ገመድ በህብረት የተሠራ በመሆኑ ሊቆርጡት ከማሰብ ውጭ ሊቆረጥ አይችልም፡፡ ይህ ስለመኾኑ ታሪክ ያስረዳል፡፡
ኢትዮጵያን ወርረው ሕዝቦቿን አንገት ሊያስደፉ የጣሩ የውጭ ኀይሎችና የውስጥ ባንዳዎች ባለፉት ዘመናት ሞክረውት በግልባጩ ሀፍረትን እና ሽንፈትን ተከናንበው መመለሳቸው በታሪክ ድርሳናት ተከትቦ ሁሌም ሲታወስ የሚኖር ነው፡፡
ወደቀች ስትባል ከፍ የምትለው ኢትዮጵያ በሕዝቦች መካከል ልዩነት ፈጥሮ ማሸነፍ የተሳነው ጠላት አሁን ደግሞ ሌላውን የመጫወቻ ካርድ ስበው እርስበርስ በማባላት በፍርስራሿ ላይ ሊጫወቱ ሞክረዋል፡፡ ይህ ግን እንደማይኾን ያውቁታል፡፡ ግን ደግሞ እድላቸውን ለመሞከር አሁንም የመጫወቻ ካርዳቸው መሳብ ቀጥለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ጠላቶች ሕዝቦቿን ለማባላት ብዙ ስልቶች ቢኖራቸውም የሀገሪቱን ታላላቅ እምነቶች ማለትም ክርስትና እና እስልምናን ለማጋጨት በተደጋጋሚ ሲሞክሩ ይስተዋላል፡፡ ይሁን እጅ የሁለቱ ሃይማኖቶች በኢትዮጵያ ያላቸው ስሪት ጥብቅ በመኾኑ ሊሳካላቸው አይችልም፤ መቸም ቢኾን አይሳካላቸውም፡፡
የሁለቱን ሃይማኖቶች አብሮነት ለመረዳት ወደ ሕዝብ ወርዶ ስብጥሩን የአኗኗር ሁኔታውን ማየት ያስፈልጋል፡፡
ሐጅ ማሕመድ ሰብዲን ዳውድ ከአሚኮ ጋር በነበራቸው ቆይታ ሁለቱ እምነቶች በማኅበራዊ ሕይዎት የተሳሰሩ በመኾናቸው ለመለየት ያዳግታል ባይ ናቸው፡፡ ልብ ብለው ከተመለከቱ እና በእያንዳንዱ የኢትዮጵያ ክፍል ቢገቡ የሕዝቡን የመረዳዳት እና የአብሮነት ኑሮ በእድሩ ሲጠብቅ እና ላይለያይ ተዋህዶ ታየዋለህ ይላሉ፡፡
“ሐጅ ማሕመድ ሰብዲን ዳውድ እስኪ ንገረኝ በዚህ ማኅበራዊ ህይዎት ውስጥ ያለን ሕዝብ እንዴት አድርገህ ትለየዋለህ ትሞክር ይኾናል እንጅ አይሳካም” ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያዊያን ክርስቲያኖች እና ሙስሊሞች ሌላው ያስተሳሰራቸው ገመድ በሰርግ ጊዜ ያለው መስተጋብር እንደኾነ የሚያነሱት ሐጅ ማሕመድ ሰብዲን ሁለቱም የእምነት ተከታዮች የልጃቸውን ዓለም ለማየት ሲያስቡ አንዱ ሌላውን ትቶ ሰርግ ማሰብ ስለማይቻለው እኩል ተጨንቆ ደስታውን በጋራ ያደርጋል ታዲያ ይህ ማኅበረሰብ እንዴት ልትለየው ትችላለህ ትሞክር ይሆናል እንጅ መጨረሻህ በሽንፈት ነው የሚደመደመው ይላሉ፡፡
የሃይማኖታዊ በዓላት ሲቃረብ አንዱ ለሌላው ቦታ የማመቻቸት እና እርስ በእርስ ተሳስቦ የማምለኪያ ሥፍራዎችን የማጽዳት ሥራ ማከናወን የቆየው የሁለቱ ሃይማኖቶች መገለጫ ነው የሚሉት ሐጅ ማሕመድ ሰብዲን ይህን ፈሪሃ ፈጣሪ ያለውን ሕዝብ ለማጋጨት ቢሞከር እንጅ ፈጽሞ የማይኾን እንደኾነ ሊታወቅ ይገባል ባይ ናቸው፡፡
የሁለቱ ሃይማኖቶች ትስስር ሌላው መገለጫ የቤተክርስቲያን እና የመስጊዶች ግንባታ መቀራረብ ነው ያሉን ሐጅ ማሕመድ ሰብዲን በሁለቱ እምነቶች ማምለኪያ ሥፍራ አጥር ብቻ የሚለያቸው እንዳሉ ገልጸው ይህ ሃይማኖቶቹ ምንያህል እንደሚቀራረቡ የሚያረጋግጥ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በምሥጋናው ብርሃኔ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleከሃይማኖት አስተምህሮ ውጭ የሚስተዋል ድርጊትን እንደሚያወግዙ የደሴ ከተማ የሐይማኖት አባቶችና ህዝባዊ ተቋማት ሕብረት አስታወቁ።
Next articleሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ የሚፈጸሙ ሕገ ወጥና የወንጀል ተግባራትን መንግሥት እንዲያስቆም የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠየቀ፡፡