
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 21/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት 1 ሽህ 443ኛ ሂጅራ ኢድ አልፈጥር በዓልን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡
የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ሼህ ሰኢድ ሙሃመድ የረመዳን ወር ያለው ከሌለው የሚደጋገፍበት፣ ወሩን ሙሉ ቁርዓን የሚቀራበት፣ መልካም ባሕሪያትና ሥራዎች ጎልተው የሚታዩበት ወር እንደኾነ አንስተዋል፡፡
የረመዳንን ወር ከሌሎች ወራቶች በበለጠ በመልካም ሥነ ምግባር እንዳሳለፍነው ኹሉ በየትኛውም የሕይወት እንቅስቃሴ የተለመደ አድርጎ መቀጠል ይገባል ብለዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ የኢድ አልፈጥር በዓልን ስናከብር ከኢድ ሶላት በፊት ግዴታ የኾውን ዘካ በማውጣት ለሚገባቸው በመስጠት ሊኾን ይገባል ብለዋል፡፡
ከኢድ ሶላት በኋላም የተቸገሩትን በማብላት እና በማጠጣት እንዲኹም ለሀገራችን ሰላም ዱአ በማድረግ ልናከብረው ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
ሼህ ሰኢድ ሰሞኑን የተከሰተው ችግር የሀገራችንን የብዝሃነት ተምሳሌትነት የማይመጥን እንደኾነ ጠቅሰዋል፡፡
የክልሉ እና የፌዴራል መንግሥታት በአጥፊዎቹ ላይ አስፈላጊውን እርምጃ በመውሰድ ሀገርን ከጥፋት የማዳን መንግሥታዊ ኀላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡ መላው የኅብረተሰብ ክፍልም ሰላም የመጀመሪያም የመጨረሻም አማራጭ መኾኑን በመገንዘብ ኹሉም ለሰላም ዘብ መቆም እንደሚገባው ነው ፕሬዚዳንቱ ያሳሰቡት፡፡
የኹሉም ሃማኖቶች ተከታዮች ለረጅም ጊዜ በፍቅር የኖሩ መኾኑን ያነሱት ፕሬዚዳንቱ በሚፈጠሩ ጥቃቅን ችግሮች ላይ ቤንዚን በማርከፍከፍ ችግር ለሚጥሩ ኀይሎች ዓላማ ማሳኪያ መኾን እንደማይገባ መክረዋል፡፡ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶችም ማኅበረሰቡን ማስተማር እንዳለባቸው ጠይቀዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ዳግማዊ ተሠራ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/