የኢድ አልፈጥር በዓልን በሰላም ለማክበር በቂ ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን የአማራ ክልል ፖሊሰ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

216

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 21/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ለአንድ ወር በጾም እና ዱዓ ሲከበር የነበረው የሮመዳን ጾም ሊጠናቀቅ ቀናት ቀርተውታል፡፡ የሮመዳን ወር ጾም ፍጻሜ የሆነው የኢድ-አልፈጥር በዓልም ከሰሞኑ ይከበራል፡፡ በዓሉ በሰላም ተጀምሮ በሰላም እንዲጠናቀቅ በቂ የፀጥታ ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

ከሰሞኑ በሕዝበ ክርስቲያኑ ዘንድ የተከበረውን የትንሣኤ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ የፀጥታ ኃይሉ እቅድ አዘጋጅቶ ሲሠራ መቆየቱን በአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የማኅበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል መምሪያ ኅላፊ ኮማንደር ጀማል መኮንን አንስተዋል፡፡
ኮሚሽኑ በእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ የሚከበረውን የኢድ-አልፈጥር በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ የሚያስችል እቅድ አዘጋጅቶ እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የክልሉን ሠላም በመጠበቅ በኩል ከፖሊስ ኃይል ጎን አጋዥ የኾኑ የፀጥታ ኃይሎች በቅንጅት ስምሪት ወስደው እየሠሩ መኾናቸውን ኮማንደር ጀማል አስታውቀዋል፡፡ ሕዝቡ ራሱ የሰላሙ ዘብ እና ጠባቂ እንዲኾንም እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡ ኢድ-አልፈጥር በመስጅድ እና በጎዳና ላይ አፍጥር አማኞች በጋራ ወጥተው የሚያከብሩት በመኾኑ የተለየ የፀጥታ ስምሪት እና ዝግጅት ያስፈልገዋል ያሉት ኮማንደሩ ለዚኽም በቂ የፀጥታ ኃይል ስምሪት ተደርጓል ብለዋል፡፡

ከሰሞኑ የተፈጠሩት የፀጥታ ችግሮች ተጨማሪ ዝግጅት እና ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ያሳዩ መኾናቸውን ነው ኮማንደር ጀማል የጠቆሙት፡፡ ፖሊስ ችግሮች እንዳይፈጠሩ ቀድሞ መከላከል ላይ ትኩረት ያደረገ የፀጥታ ሥራዎችን እያከናወነ ነው ብለዋል፡፡

ኮማደር ጀማል ፖሊስ እና የፀጥታ ኅይሎች የትኛውንም ዓይነት ዝግጅት ቢያደርጉ የሕዝብ ተሳትፎ ከሌለው የሚፈለገውን ውጤት እንደማያመጣ ገልጸው ሕዝቡ ከፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት እንዲሠራም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ችግሮች ሲፈጠሩ መረጃ በመስጠት፣ ቀድሞ በመከላከል እና ለፀጥታ ኃይሉ እንቅስቃሴ ምቹ ኹኔታዎችን በመፍጠር ሕዝቡ የድርሻውን እንዲወጣ ኮማንደር ጀማል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ኢትዮጵያውያንን የጋራ መተባበር እና መደጋገፍ እሴት በጠበቀ መልኩ በዓሉን ማክበር እንደሚጠበቅ ነው ኮማንደር ጀማል ያሳሰቡት፡፡ በተለይም ወጣቶች በመከባበር እና በመደጋገፍ በመሥራት የክልሉን ሰላም የመጠበቅ ግዴታ አለባቸው ብለዋል፡፡ ከፀጥታ ኀይሉ ጎን በመሰለፍ አብረው እንዲሠሩም ኮማንደር ጀማል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“ክልሉን የትርምስ ቀጣና ለማድረግ የሽብር ድርጊት በሚፈጠሩ አካላት ላይ የማያዳግም እርምጃ እንወስዳለን” ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)
Next articleቺርቤዋ ማንዚ 15-8-2014 ም.አ(አሚኮ)