“ክልሉን የትርምስ ቀጣና ለማድረግ የሽብር ድርጊት በሚፈጠሩ አካላት ላይ የማያዳግም እርምጃ እንወስዳለን” ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)

310

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 20/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) በጎንደር ከተማ የተፈጠረውን ክስተት አስመልክቶ እንዳሉት
የክልሉ መንግሥት ተገቢውን ክትትል አድርጎ የማያዳግም እርምጃ ይወስዳል።

እንደ ሀገር ከገጠሙን ችግሮች ሙሉ በሙሉ ሳንላቀቅ ሃይማኖትን ምክንያት በማድረግ የእርስ በርስ ግጭት ለመፍጠር የሚታትሩ እኩይ አካላትን አንታገስም ሲሉ ርእሰ መሥተዳድሩ አስታውቀዋል።

ዶክተር ይልቃል “ክልሉን የትርምስ ቀጣና ለማድረግ የሽብር ድርጊት በሚፈጠሩ አካላት ላይ የማያዳግም እርምጃ እንወስዳለን” ብለዋል፡፡

ይኽ ሙከራ ኢትዮጵያን ካለችበት ነባራዊ ኹኔታ ለባሰ ቀውስ የሚዳርግ በመኾኑ ድርጊቱ ሊወገዝ ይገባዋል ነው ያሉት።

የክልሉ መንግሥት ተገቢውን ክትትል አድርጎ እርምጃ ይወስዳል ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ወጣቶች ለሰላም ዘብ እንዲቆሙም አሳስበዋል።

ዘጋቢ፡- ጋሻው አደመ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየሲዳማ ሕዝብ ዘመን መለወጫ ፊቼ ጫምባላላ በዓል በይፋ ተከፈተ።
Next articleየኢድ አልፈጥር በዓልን በሰላም ለማክበር በቂ ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን የአማራ ክልል ፖሊሰ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡