የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በማኅበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጩ ጠብ አጫሪ መልዕክቶችን አወገዘ።

349

ሚያዝያ 20/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በጎንደር ከተማ የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ በማኅበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጩ ጠብ አጫሪ መልዕክቶችን ማውገዝ እንደሚገባ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አሳስቧል፡፡

ጉባኤው በጎንደር ከተማ የተከሰተውን የፀጥታ ችግር በተመለከተ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

የጉባኤው ጠቅላይ ጸሓፊ ቀሲስ ታጋይ ታደለ በሰጡት መግለጫ ለዘመናት ተከባብረው በኖሩ ሕዝቦች ላይ የተፈጠረውን ግጭት አውግዘዋል፡፡ የኹሉም ቤተ እምነት ተከታዮች እንደ ሃይማኖቶች አስተምሕሮ መረጋጋትና ሰላምን ማስፈን እንዳለባቸው ገልጿል፡፡

ድርጊቱ ፈጽሞ የኹለቱን የእምነት ተከታዮች የማይወክልና ሊወገዝ የሚገባ ነው ተብሏል፡፡

መንግሥት ጉዳዩን አጣርቶ ለወንጀለኞች ተገቢውን ፍርድ መስጠት እንዳለበት ተመላክቷል፡፡

በታሪካዊቷ ከተማ የተከሰተው ግጭት ለዘመናት አብረው የኖሩትን የኹለቱንም እምነት ተከታይ ሕዝብ ክብርና መተሳሰብ የማይወክል መኾኑን ኹሉም ኅብረተሰብ ሊረዳው ይገባልም ተብሏል፡፡

ዋልታ እንደዘገበው የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በተፈጠረው ክስተት ማዘኑን በመግለፅ ሁሉም የእምነት አባቶች ለሰላም ሊሰሩ እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ #ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ #ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ። https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በሚያነሷቸው የተለያዩ ችግሮች ከከተማው መስተዳድር ምክር ቤት ጋር ተወያይተዋል።
Next articleየሕዝብን ሰላምና ደኅንነት በሚያውክ አካል ላይ አስፈላጊው እርምጃ እንደሚወሰድ የአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኀላፊ ደሳለኝ ጣሰው ተናገሩ። በጎንደር የተፈጠረውን ችግር ለማባባስ የሚጥሩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም አቶ ደሳለኝ አሳስበዋል።