
ጎንደር: ሚያዝያ 19/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በጎንደር ከተማ በትላንትናው ዕለት በሃይማኖት ሽፋን የተፈጠረው ችግር ማንንም የማይወክል ነው ሲል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤው ድርጊቱን አውግዟል፡፡
የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በመግለጫዉ የተፈጠረዉ ግጭት የኹለቱንም ሃይማኖት አማኞችን የማይወክልና በሌሎች አካላት የተቀነባበረ ሴራ እንደኾነ ገልጿል።
ድርጊቱም ጎንደርን ለማወክና ለማበጣበጥ የታሰበ እንደኾነ ነው በመግለጫው የጠቀሰው፡፡
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ አባ ዮሴፍ ደስታ እንደተናገሩት በጎንደር ከተማ የተከሰተው ግጭት ሰላምን በማይሹ፣ ለሰላም ዋጋ በማይሰጡ ሰዎች የተፈጠረ ችግር ነው፤ ይህንን ችግር ደግሞ ለዘመናት በአብሮነት የሚኖሩ የኹለቱ ሃይማቶች በጋራ መታገል እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡
ቤተክርስቲያኒቱ ለሰላም ትሠራለች ያሉት አባ ዮሴፍ ደስታ ችግሩ በውይይትና በመነጋገር እንዲፈታም ይሠራል ብለዋል፡፡
የጎንደር ወንጌላዉያን አብያተክርስቲያናት አገልጋይ አማን ሷሊህ በበኩላቸው ግጭት ለማስነሳት የሞከሩ አካላት በእምነት ሽፋን ድብቅ የፖለቲካ አጀንዳን ለማራመድ የሚሹ ናቸው ብለዋል።
የኹለቱም ሃይማኖቶች አስተምህሮ ይህንን አይፈቅድም ሲሉ አውግዘዋል።
የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤው ለሰው ሕይዎት መጥፋትና ለንብረት መውደም ምክንያት የኾኑ ግለሰቦችን መንግሥት በፍጥነት ለሕግ ማቅረብ ይገባዋል ነው ያሉት፡፡
አሁን ላይ በከተማዋ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዳለ የገለጹት የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አባላቱ በቀጣይ ኹለቱም ሃይማኖቶች ለሰላም ትኩረት በመስጠት የጎንደር የቀደመ አብሮ የመኖርና የመቻቻል ባሕልን ማጠናከር እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ደስታ ካሳ-ከጎንደር
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/