“የአማራና የአፋር ሕዝብ የረጅም ዘመን የአብሮነት ታሪካዊ ትስስር ያለው ነው” የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ታደሰ ገብረጻዲቅ

87

አፋር: ሚያዝያ 19/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር በአፋር ክልል ዞን 5 ለሶሙሮቢ ገላሎ ወረዳ አስተዳደር ሕዝብ ከ740 ሺህ ብር በላይ የሚገመት የተለያዩ ቁሳቁስና የምግብ እህል ድጋፍ አድርጓል።

በሶሙሮቢ ገላሎ ወረዳ አስተዳደር ኩማሜ ከተማ ሚያዝያ 3/2014 ዓ.ም በተከሰተ የእሳት አደጋ 80 የንግድ ሱቆችና 90 መኖሪያ ቤቶች ወድመዋል።

በሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ታደሰ ገብረ ጻዲቅ የተመራ የዞኑና የቀወት ወረዳ አስተዳደር ልዑክ በቦታው በመገኘት የጉዳቱን ሁኔታ በመመልከት የመጀመሪያ ዙር የምግብ እህልና የቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል።

አቶ ታደሰ የአማራና የአፋር ሕዝብ የረጅም ጊዜ አብሮ የመኖር የመደጋገፍና የመረዳዳት ታሪካዊ አንድነት ያለው ሕዝብ ነው ብለዋል።

በተፈጠረው ድንገተኛ የእሳት አደጋ በደረሰው የንብረት ውድመት ማዘናቸውን ገልጸው የተጎዱ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም የሰሜን ሸዋ አስተዳደርና ሕዝብ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

ድጋፉን የተረከቡት የሶሙሮቢ ገላሎ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሀሰን ሀንዲዬ አደጋው በደረሰ ማግስት የቀወት ወረዳ አስተዳደር ፈጥኖ በመድረስ ድጋፍ በማድረግ ከጎናቸው እንደነበረ ገልጸዋል።

ዛሬም የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ባደረገላቸው ድጋፍ መደሰታቸውን ገልጸው የሁለቱ ክልል ሕዝቦች የዘመናት አብሮነት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

አስተያየታቸውን ለአሚኮ የሰጡ የኩማሜ ከተማ ነዋሪዎችም በችግራችን ወቅት አብሮነቱን በተግባር ያሳየንን የሰሜን ሸዋ አስተዳደርና ሕዝብን እናመሰግናለን ብለዋል።

ዘጋቢ:–ሥነ-ጊዮርጊስ ከበደ
ከኩሚሜ ከተማ (አፋር)

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“በምሥራቅ አፍሪካ የሚፈጠሩ ግጭቶችን ለመከላከል የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዐቶችን ማበጀት ይገባል” የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ.ር)
Next articleበሃይማኖት ሽፋን በሕዝብ መካከል ግጭት የሚፈጥሩ አካላትን መታገል እንደሚገባ የጎንደር ከተማ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ገለጸ፡፡