“በምሥራቅ አፍሪካ የሚፈጠሩ ግጭቶችን ለመከላከል የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዐቶችን ማበጀት ይገባል” የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ.ር)

162

ሚያዝያ 19/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የምሥራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኀይል ስትራቴጂክ ከፍተኛ የአማካሪዎች መድረክ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ነው፡፡

በዝግጅቱ ላይ የኢፌዴሪ የመከላከያ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ.ር) እንደተናገሩት በምሥራቅ አፍሪካ የሚፈጠሩ ግጭቶችን ለመከላከል የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዐቶችን ማበጀት ይገባል። ለዚህም የምሥራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኀይል ስትራቴጂክ ከፍተኛ የአማካሪዎች ሚና ከፍተኛ መኾን እንደሚገባው ተናግረዋል፡፡

የምሥራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኀይል የስትራቴጂክ ከፍተኛ የአማካሪዎች ቡድንን እንደ ተቋም ማደራጀቱ ለሰላም ግንባታ ሥራ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው የገለጹት ሚኒስትሩ አፍሪካውያን ያሉንን በጎ እሴቶችና ባህላዊ የግጭት አፈታት ዘዴዎችን በመጠቀም ለሰላም መረጋገጥ ማዋል ይገባልም ብለዋል፡፡

የምሥራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኀይል ዋና ዳይሬክተር ብርጋዴር ጄነራል ጌታቸው ሽፈራው፥ በቀጠናው የሚታዩ የፀጥታ ችግሮችን ለመከላከል የተለያዩ አበረታች ሥራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።

በቀጣናው ግጭቶች ሳይፈጠሩ ቀድሞ ለመከላከል የሚያስችል ስልት ተነድፎ እየተሠራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

የቀድሞ የቡሩንዲ ፕሬዚዳንት ዶሚቲን ንዳይዜ ጨምሮ ከአስሩ የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ የቀድሞ አምባሳደሮችና ከፍተኛ የጦር አመራሮች ተገኝተዋል።

በመድረኩ በቀጣናው የሚፈጠሩ ግጭቶችን ለመከላከል በሚቻልበት ዘዴ ላይ ምክረ ሐሳቦች ይቀርባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከመከላከያ ሠራዊት የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየፖለቲካ ፓርቲዎች ሀገራዊ ምክክሩ ስኬታማ እንዲኾኑ ኮሚሽኑ በቀጣይ በሚያካሂዳቸው ተግባራት ላይ እገዛ በማድረግ የበኩላቸውን ሚና ለመወጣት ዝግጁ መኾናቸውን ገለጹ።
Next article“የአማራና የአፋር ሕዝብ የረጅም ዘመን የአብሮነት ታሪካዊ ትስስር ያለው ነው” የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ታደሰ ገብረጻዲቅ