
ደብረ ማርቆስ: ሚያዝያ 19/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤና የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ አባላት በደብረ ማርቆስ ከተማ በንጋት ኮርፖሬት እየተገነባ የሚገኘውን ማዕድ የምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካን የግንባታ ሂደት ተመልክተዋል፡፡
በምክር ቤቱ የበጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ዓለም ዋጋየ የፋብሪካው ግንባታ መዘግየት በሚካሄዱ የምክር ቤት ጉባኤዎች ላይ በየጊዜው ጥያቄ ይነሳበት የነበረ ጉዳይ መሆኑን ገልጸው አሁን ላይ ያለው የግንባታ ሂደት መልካም መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋንቱ ተስፋዬ የፋብሪካው የግንባታ ደረጃ ከዚህ መድረስ ተስፋ ሰጭ ነው፤ ግንባታው ተጠናቆ ወደ ሥራ እንዲገባም ሰፊ ክትትል ያስፈልገዋል ብለዋል፡፡
ፋብሪካው የአካባቢውን አርሶ አደሮች ተጠቃሚ ለማድረግ ትልቅ ተስፋ ያለው መሆኑንና ተጠናቆ ወደ ሥራ እንዲገባ ምክር ቤቱ የሚጠበቅበትን ድጋፍ እንደሚያደርግ አፈጉባኤዋ አስታውቀዋል፡፡
የንጋት ኮርፖሬት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ባምላኩ አስረስ የፋብሪካው ግንባታ በተለያዩ ምክንያቶች የዘገየ መሆኑን ገልጸዋል።
ፋብሪካው ከጥቅምት 2015 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሥራ እንደሚገባና በዓመት ውስጥ 75 ሺህ ቶን እና በቀን 250 ቶን የስንዴ ምርትን በግብዓትነት በመጠቀም ፓስታ፣ ማካሮኒ፣ ብስኩትና እና 1ኛ ደረጃ የስንዴ ዱቄት ማምረት የሚችል ነው ተብሏል።
ፋብሪካው ከ700 በላይ ለሚሆኑ ወገኖች የሥራ እድል እንደሚፈጥርም ታውቋል፡፡
ዘጋቢ:–ንጉስ ድረስ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/