
ሚያዝያ 19/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ብልፅግና ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤውን በተመለከተ ተጨማሪ ሰነዶች እና መረጃዎችን እንዲያቀርብ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጠይቋል።
ቦርዱ ሚያዝያ 13 ቀን 2014 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ፓርቲው ያቀረባቸውን የጠቅላላ ጉባኤ ሰነዶች እና ጠቅላላ ጉባኤውን በታዘቡት የቦርዱ ተወካዮች የቀረበውን ሪፖርት መመርመሩን አስታውቋል።
ይሁንና የጠቅላላ ጉባኤውን ሂደት፣ በጉባኤው የተላለፉ ውሳኔዎች እና
የተደረጉ ምርጫዎችን በተመለከተ ከሕጉ አንጻር ለመወሰን ተጨማሪ ሰነዶች እና መረጃዎችን ማየት አስፈላጊ መሆኑን ጠቁሟል።
በሆኑም ፓርቲው ምርጫ ቦርድ በዝርዝር ያስቀመጣቸውን ጉዳዮች ከሚያዚያ 25 ቀን 2014 ዓ.ም በፊት ለቦርዱ እንዲያቀርብ አሳውቋል።
ቃለ ጉባኤን በተመለከተ፣ በጠቅላላ ጉባኤ ቃለ ጉባኤው ላይ የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባው ምልዓተ ጉባኤ ተሟልቷል ቢባልም በግልፅ የጠቅላላ ባኤው ተሳታፊ አባላት ብዛት ስላልተቀመጠ ተገልፆ እንዲቀርብ፤
የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት የተጠቆሙበት ሂደት፣ እነማን እንደተጠቆሙ፣ ከተጠቆሙት ውስጥ የተመረጡት አባላት እያንዳንዳቸው
በስንት ድምፅ እንደተመረጡ በጠቅላላ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ ውስጥ ያልተገለፀ በሆኑ መረጃው ተካትቶ እና ተረጋግጦ እንዲቀርብ፤
በፓርቲው የቀረበው ጠቅላላ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ በፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ
ኮሚቴ ተፈርሞ እንዲቀርብ፤
የማዕከላዊ ኮሚቴው ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትን የመረጠበትን ሂደት
የሚያሳይ የማዕከላዊ ኮሚቴ ቃለ ጉባኤ ስላልቀረበ እንዲቀርብ ምርጫ ቦርድ ጠይቋል።
የፖርቲው መተዳደሪያ ደንብን በተመለከተ በመተዳደሪያ ደንብ አንቀፅ 18/3 መሠረት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ብዛት እና ስብጥርን በተለከተ የወጣ የአፈፃፀም መመሪያ ካለ የመሪያውን ኮፒ ማዕከላዊ ኮሚቴው መመሪያውን ካፀደቀበት ቃለ ጉባኤ ጭምር እንዲቀርብ ምርጫ ቦርድ ለፓርቲው በጻፈው ደብዳቤ ጠይቋል።
መረጃው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ነው።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/