
ጎንደር :ሚያዝያ 19/2014 ዓ.ም (አሚኮ)
በጎንደር ከተማ አስተዳደር ፋሲል ክፍለ ከተማ እና በላይ አርማጭሆ ወረዳ አስተዳደር በሚገኙ የኩታ ገጠም ቀበሌዎች ያሉ የመንግሥት ሠራተኞች የአካባቢያቸውን የሰላም እንቅስቃሴ ዘላቂ በማድረግ ረገድ በትኩረት እንደሚሠሩ ገልጸዋል፡፡
የምክክሩ ተሳታፊዎች የጎንደርና አካባቢው ሕዝብ ተቻችሎ፣ ተከባብሮና ተሳስቦ ለዘመናት እየኖረ ያለ መኾኑን አንስተዋል፡፡ ነገር ግን ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ጥቂት ጥቅመኞች የአካባቢውን ሰላም ረፍት ለመንሳት እየሠሩ እንደሚገኙ አስንስተዋል።
የተዋለዱ እና ጠንካራ ማኅበረሰባዊ ውቅር ያላቸውን የቅማንትና የአማራ ሕዝቦች በማጋጨት ለሰው ሕይወት መጥፋትና ለንብረት መውደም ምክንያት እንደኾኑም አንስተዋል።
አሁንም ሃይማኖትን ሽፋን አድርገው የጎንደርን ሰላም ለማደፍረስና ሀገር ለማተራመስ የሚደረገውን ጥረት ሆን ተብሎ የተወጠነ ሴራ መኾኑን ተወያዮቹ አንስተዋል፡፡ ይኽ ዓይነቱ እኩይ ተግባር ተቀባይነት የሌለው እና ሕዝብን የማይወክል መኾኑንም ነው የገለጹት።
እየታዩ ያሉ የሰላም እጦቶች በዋናነት ፖለቲካ ወለድና ሰው ሰራሽ ናቸው ያሉት የውይይቱ ተሳታፊዎች በመመካከርና በመረዳዳት ለአካባቢያቸው ሰላም ዘብ እንደሚቆሙ አስታውቀዋል።
ለጋራ ችግር የጋራ መፍትሔ ለመስጠትም ተከታታይ ውይይቶችን ማድረግ፣ ለጠላት የማይመች አካባቢ መፍጠር፣ ለግል ጥቅማቸው ብጥብጥን አማራጭ የሚያደርጉ ጥቅመኞችን አሳልፎ በመስጠት የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ነው ተወያዮቹ ያስታወቁት።
የአካባቢውን ሰላም በዘላቂነት በማረጋገጥ ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማስፋት ችግርን በውይይት ለመፍታት የሚደረገው ጥረት በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የፋሲል ክፍለ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አቶ ባንተ ወጋየሁና የጎንደርና አካባቢው ሰላም ሸንጎ ሰብሳቢ አቶ አዳነ ዓለምሰገድ አስረድተዋል።
ዘጋቢ፡-ኃይሉ ማሞ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/