
የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት ጋር በዳረገው ስምምነት መሠረት ነው በእስር ላይ የነበሩ 400 ኢትዮጵያዊያን ዛሬ ጥቅምት 5/2012 ዓ.ም ወደ ሀገራቸው የተመለሱት፡፡
ኢትዮጵያውያኑ ቀይ ባህርን አቋርጠዉ ሲጓዙ በሳዑዲ ዓረቢያ የጸጥታ ሀይል ተይዘው በእስር ላይ የቆዩ ናቸው ተብሏል።
የዛሬዎቹን ተመላሾች ጨምሮ በበጀት ዓመቱ ባለፉት 3 ወራት ውስጥ 32 ሺህ 890 ኢትዮጵያውያን ከተለያዩ ሀገራት ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል ብሏል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፡፡
ምንጭ፡- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት