በጎንደር ከተማ በነጻ ማሕበረሰባዊ ግልጋሎታቸው የሚታወቁት ሸህ ከማል ለጋስ አረፉ።

297

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 18/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በሊቅነታቸውና በነጻ ማሕበረሰባዊ ግልጋሎታቸው ይታወቃሉ። ለ40 ዓመታት ባህላዊና መንፈሣዊ ህክምና፣ በሙሉ ጊዜያቸው በነጻ ሲሰጡ ቆይተዋል። የሙስሊም ክርስቲያን አባትም ነበሩ። የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድም “አባ ለጋሥ” ተብለው ይታወቃሉ።

ትውልድና ዕድገታቸው ጎንደር ከተማ ነው። ከቀደምት የሐበሻ ሊቃውንት በርካታ የዕውቀት ዘርፎችን የቀሰሙ፣ በአባታቸው በአባ ሼህ ለጋሥ የተመረቁ እና በእርሳቸው ሥፍራ ተተክተው መንፈሣዊ ህክምና በነጻ ሲሰጡ የቆዩ ናቸው።

ከመንፈሣዊና ባህላዊ ህክምና ባሻገር ሕዝብን የሚያሸማግሉ፣ የማሕበረሰብን መንፈሣዊ ጉድለት የሞሉ፣ የነበረውን የአብሮነት እሴት አብዝተው ያጠናከሩ፣ ሁለንተናዊ አበርክቶ ለማሳረፍ የቻሉ ናቸው። ለሀገር እና ለወገን አዘውትረው ዱዓ በማድረግ ሰፊ ሱታፌ ነበራቸው። ነዳያንን እና መሳኪኖችን በመመፅዎትና በማስታወስ ይታወቃሉ።

የቀደምት የሐበሻ ሊቃውንትን መንፈሣዊ ትውፊትና እሴት በማስቀጠል በኩልም የጎላ ሚና አበርክተዋል። መንዙማ፣ መውሊድ፣ ሰደቃ ለትውልድ እንዲተላለፉ አድርገዋል።

ለሳምንት በቆየ ድንገተኛ ህመም፣ በቤታቸው የሕክምና ክትትል ሲደረግላቸው ቆይተው በተወለዱ በ84 ዓመታቸው ዛሬ አርፈዋል።

ሥርዓተ-ቀብራቸው በጎንደር ከተማ ዛሬ ይከናወናል። ለቤተሰቦቻቸው እንዲኹም ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን እንመኛለን። መረጃው የጎንደር ከተማ ኮምዩኒኬሽን ነው

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleበእንግሊዙ ዘጋርዲያን ጋዜጣ ለማጭበርበሪያነት የዋለው የዋግኽምራ ተፈናቃይ እናቶች ምስል እውነታ ተጋለጠ።
Next articleየሽውኃው ጊዮርጊስን የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን የደቡብ ጎንደር ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪ አስታወቀ።