በእንግሊዙ ዘጋርዲያን ጋዜጣ ለማጭበርበሪያነት የዋለው የዋግኽምራ ተፈናቃይ እናቶች ምስል እውነታ ተጋለጠ።

425

ሚያዝያ 18/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የጌቲ ኢሜጅስ የፎቶ ጋዜጠኛ ጀማል ኮንተስ ሰቆጣ ላይ ያነሳውን የዋግኽምራ ተፈናቃይ እናቶችን ምስል የእንግሊዙ ዘጋርዲያን በትግራይ ክልል የኢትዮጵያ መንግሥት የፈጸመው በደል በማስመሰል የተጎዱ እናቶችን ምስል ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በተሳሳተ መረጃ በመጠቀም ማጭበርበሩን አጋለጠ፡፡

የጌቲ ኢሜጅስ ጋዜጠኛው ጀማል ኮንተስ ያነሳው ምስል፥ አሸባሪው ሕወሓት በአማራ ክልል ዋግኽምራ ከፈጸመው የሽብር ጥቃት ሸሽተው በሰቆጣ መብራት ኃይል ጣቢያ የተጠለሉትን ተፈናቃይ እናቶች መኾኑን በትዊተር ገጹ አስፍሯል፡፡

ምስሉንም በዚህ ዓመት በፈረንጆቹ መጋቢት 30 ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ይፋ እንዳደረገው አመላክቷል።

ነገር ግን ዘጋርዲያን ይህንን ምስል የተጠቀመው “በትግራይ ክልል ያለውን ሁኔታ” በተሳሳተ መልኩ ለማሳየት እና ዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ለማጭበርበር ነው ሲል የፎቶ ጋዜጠኛው አጋልጧል፡፡

ዘጋርዲያን የፈጸመውን አሳፋሪ ተግባርም አሜሪካዊቷ ጋዜጠኛ አን ጋሪሰን ኮንናዋለች፤ ጀማል ኮንተስ ፎቶውን ሲያነሳ አብራው በሰቆጣ መጠለያ ጣቢያ እንደነበረችም በትዊተር ገጿ ምስክርነቷን ሰጥታለች፡፡

እንደ ፋብኮ ዘገባ ምስሉ በትግራይ ክልል ውስጥ ያሉትን እናቶች ሳይኾን የሚያሳየው አሸባሪው ሕወሓት በአማራ ክልል ዋግኽምራ ላይ ከፈጸመው ወረራ ራሳቸውን ለማዳን ሸሽተው በሰቆጣ የሰፈሩትን ተፈናቃይ እናቶች ነው ስትልም ዕውነቱን በትዊተር ገጿ አስፍራለች፡፡

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleበመድኃኒት አቅርቦት እየተፈተነ ያለው የተፈራ ኃይሉ መታሰቢያ አጠቃላይ ሆስፒታል የድጋፍ ጥሪ
Next articleበጎንደር ከተማ በነጻ ማሕበረሰባዊ ግልጋሎታቸው የሚታወቁት ሸህ ከማል ለጋስ አረፉ።